የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የመታሰቢያው በዓል በተከበረበት በሚያዝያ ወር ባከናወንነው አገልግሎት በጣም ተደስተናል። በዚህ ወር 9,845 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝተናል፤ ከእነዚህ አስፋፊዎች መካከል 2,086 የሚሆኑት በረዳት አቅኚነት አገልግሎት ተካፍለዋል! በመታሰቢያው በዓል ላይ ደግሞ 25,896 ሰዎች ተገኝተዋል፤ ይህም የእኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ሰዎች እንዳሉ ይጠቁማል።