ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት
ኅዳር 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 30 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 10 ከአን. 1-9 እና በገጽ 79 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 19-22 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘዳግም 22:20-30 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኃጢአት ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው?—rs ገጽ 373 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ጉዲፈቻ—ይሖዋ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የተገኙ መንፈሳዊ የጉዲፈቻ ልጆች አሉት—w09 4/1 ገጽ 10-11 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ለአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ቃለ ምልልስ ማድረግ። በጉባኤው ውስጥ ምን ኃላፊነቶችን ትወጣለህ? የመስክ አገልግሎት ስምሪት ቡድኖችን የምትጎበኝበት ዓላማ ምንድን ነው? በቡድኑ ውስጥ ያሉት አስፋፊዎች ከጉብኝቱ ጥቅም ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው? አስፋፊዎች ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ እንድትረዳቸው በግለሰብ ደረጃ መጥተው ቢጠይቁህ ምን እገዛ ታደርግላቸዋለህ?
20 ደቂቃ፦ “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለሰዎች በግለሰብ ደረጃ አሳቢነት ማሳየት።” በውይይት የሚቀርብ። በክፍሉ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ ሁለት ክፍል ያለው ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በሠርቶ ማሳያው የመጀመሪያ ክፍል ላይ አስፋፊው ለሚያነጋግረው ሰው በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ሳይሰጥ በወሩ ውስጥ የሚበረከተውን ጽሑፍ ይሰጠዋል። ሁለተኛው ክፍል ከመጀመሪያው ክፍል ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም አስፋፊው በዚህ ጊዜ ለሚያነጋግረው ሰው በግለሰብ ደረጃ ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳያል።
መዝሙር 25 እና ጸሎት