ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት
ኅዳር 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 50 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 11 ከአን. 1-4፣ በገጽ 84 ላይ የሚገኘው የመግቢያ ሐሳብ እንዲሁም በገጽ 86 እና 87 ላይ የሚገኙ ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 28-31 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘዳግም 30:15 እስከ 31:8 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ እንስሳት ነፍሳት ናቸው—rs ገጽ 375 አን. 2 እስከ ገጽ 376 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ መዋብ—ውበትን ስለመጠበቅ ለክርስቲያኖች የተሰጠ ምክር—w09 2/15 ገጽ 20-21፤ w02 8/1 ገጽ 17-19 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ “ድረ ገጻችንን ለአገልግሎት ተጠቀሙበት—‘የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው።’” በውይይት የሚቀርብ። ድረ ገጻችን ላይ በሚገኘው በዚህ ዓምድ ሥር መልስ ከተሰጠባቸው ጥያቄዎች መካከል አንዳንዶቹን ጥቀስ። (jw.org/am ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር ተመልከት።) በክፍሉ ላይ ከቀረቡት ሐሳቦች መካከል አንዱ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በድረ ገጹ ላይ የሚገኘውን ይህን ዓምድ መጠቀም የሚቻልበት ሌላ መንገድ ካለ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ “በተደጋጋሚ ቤቱ ብሄድም ላገኘው አልቻልኩም!” በውይይት የሚቀርብ። ያነጋገርነውን ሰው በተደጋጋሚ ቤቱ ሄደን ሳናገኘው ስንቀር ተስፋ አለመቁረጣችን አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ተናገር።—ማቴ. 28:19, 20፤ ማር. 4:14, 15፤ 1 ቆሮ. 3:6
10 ደቂቃ፦ “አዲስ የምርምር መሣሪያ።” በንግግር የሚቀርብ። በምርምር መርጃ መሣሪያው መግቢያ ላይ “ምርምር ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?” በሚለው ርዕስ ሥር የተጠቀሱትን መመሪያዎች ከልስ። ይህ መሣሪያ ያሉትን የተለያዩ ገጽታዎች ጥቀስ። አንድ አስፋፊ በምርምር መርጃ መሣሪያው ሲጠቀም የሚያሳይ መነባንብ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 11 እና ጸሎት