ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 48 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 11 ከአን. 5-12 እና በገጽ 89 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 32-34 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘዳግም 32:22-35 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ከሞት በኋላ ነፍስም ሆነ መንፈስ በሕይወት አይቀጥሉም—rs ገጽ 376 አን. 3 እስከ ገጽ 378 አን. 4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ምንዝር—በአምላክ ላይ የሚፈጸም ኃጢአት ነው—lv ገጽ 128-130 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ በታኅሣሥ ወር መጽሔቶችን አበርክቱ። በውይይት የሚቀርብ። በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙት ሦስት የአቀራረብ ናሙናዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ። ከእያንዳንዱ ሠርቶ ማሳያ በኋላ፣ የቀረበው ርዕሰ ጉዳይ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ የአንዳንድ ሰዎችን ትኩረት ሊስብ የሚችለው ለምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት ወይም በቅርቡ ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግ እና/ወይም አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በማስጀመር ረገድ ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ይህን ለማድረግ ያነሳሳችሁ ምንድን ነው? ውጤታማ እንድትሆኑ የረዳችሁ ምንድን ነው? በጉባኤያችሁ ያሉ አስፋፊዎች ባለፉት ጥቂት ወራት ሪፖርት ያደረጉትን የተመላልሶ መጠየቅ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አማካኝ ቁጥር ተናገር። ሐሳብ የሰጡትን በማመስገንና ሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ በማበረታታት ክፍልህን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ ምን ውጤት አገኘን? በውይይት የሚቀርብ። አስፋፊዎች “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለሰዎች በግለሰብ ደረጃ አሳቢነት ማሳየት” በሚለው ርዕስ ላይ የቀረቡትን ነጥቦች ተግባራዊ በማድረጋቸው ምን ጥቅም እንዳገኙ ሐሳብ እንዲሰጡ ጠይቃቸው። እንዲሁም ያገኙትን ግሩም ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 20 እና ጸሎት