ታኅሣሥ 29 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 37 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 12 ከአን. 14-20 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 12-15 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ከተቀበልነው መልካም ነገር “ጥሩ ነገር” እናውጣ።—ማቴ. 12:35ሀ
20 ደቂቃ፦ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁና ለልጆቻችሁ “ጥሩ ነገር” ቀስ በቀስ አስተምሯቸው። (ማቴ. 12:35ሀ) በውይይት የሚቀርብ። የሚከተሉትን ጥቅሶች በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንና ከልጆቻችን ምን መጠበቅ እንደሚኖርብን ተናገር፦ 1 ቆሮንቶስ 13:11፤ 1 ጴጥሮስ 2:2, 3። ‘በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ወተት መቅመስ’ ሲባል ምን ማለት እንደሆነና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንና ልጆቻችን ይህን እንዲያደርጉ መርዳት የምንችለው እንዴት እንደሆነ አብራራ። በማርቆስ 4:28 ላይ የሚገኘውን መሠረታዊ ሥርዓት አብራራ። (የታኅሣሥ 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 12 ከአን. 6-8 ተመልከት።) ተሞክሮ ያለው አንድ አስፋፊ ወይም ወላጅ (እህትም ልትሆን ትችላለች) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን አሊያም ልጁን መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርግ የረዳው እንዴት እንደሆነ እንዲናገር ቃለ መጠይቅ አድርግለት።—ኤፌ. 4:13-15፤ በግንቦት 2014 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣውን የጥያቄ ሣጥን ተመልከት።
10 ደቂቃ፦ “እንግዳ ተቀባይ በመሆን ለሌሎች ‘ጥሩ ነገር’ አካፍሉ (ማቴ. 12:35ሀ)።” በውይይት የሚቀርብ። አንዳንዶች እንግዳ ተቀባይ በመሆን ምን ጥቅም ወይም ተሞክሮ አግኝተዋል? ለሌሎች በተለይ ደግሞ ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እንግዳ ተቀባይ መሆን ስለምንችልባቸው መንገዶች ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። ከሌላ ጉባኤ የመጡ ተናጋሪዎችን ምግብ ለመጋበዝ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ጥቀስ።
መዝሙር 50 እና ጸሎት