የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/15 ገጽ 3
  • ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
km 1/15 ገጽ 3

ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

ጥር 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 30 እና ጸሎት

የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦

bt ምዕ. 14 ከአን. 1-5 እና በገጽ 112 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)

ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 5-7 (8 ደቂቃ)

ቁ. 1፦ መሳፍንት 7:12-25 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ቁ. 2፦ አምኖን—ጭብጥ፦ ራስ ወዳድና በፆታ ስሜት ላይ ያተኮረ ፍቅር ከፍተኛ መዘዝ ያስከትላል—yp 187 (5 ደቂቃ)

ቁ. 3፦ ስለ ይሖዋ መማር የምንችልባቸው መንገዶች—nwt-E ገጽ 9 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)

የአገልግሎት ስብሰባ፦

የወሩ ጭብጥ፦ ‘በታላቅ ትሕትና ጌታን አገልግሉ።’—ሥራ 20:19

መዝሙር 41

10 ደቂቃ፦ በጥር እና በየካቲት ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምሥራች የተባለውን ብሮሹር በማበርከት ያገኙትን የሚያበረታታ ተሞክሮ እንዲናገሩ ጋብዝ። ይህን ብሮሹር እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ከዚያም “ወዲያውኑ መሄድ ያለብን ለምንድን ነው?” በሚለው ርዕስ ላይ ተወያዩ።

10 ደቂቃ፦ ጌታን የሚያገለግሉ ሽማግሌዎች—የመጠበቂያ ግንብ መሪ። ለመጠበቂያ ግንብ መሪው ቃለ ምልልስ ማድረግ። ያለብህ ኃላፊነት ምን ነገሮችን ያጠቃልላል? ለመጠበቂያ ግንብ ጥናት የምትዘጋጀው እንዴት ነው? ሐሳብ ለመስጠት እጅ የሚያወጡትን ሁሉ መጠየቅ የማይቻለው ለምንድን ነው? የመጠበቂያ ግንብ ጥናቱ የሚያንጽና አስደሳች እንዲሆን የሚያነበው ወንድም፣ ተሳትፎ የሚያደርጉትና የድምፅ መሣሪያ የሚያዞሩት ወንድሞች ምን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ? ይህን አስፈላጊ ኃላፊነት በመወጣት ረገድ በቅርብ የተደረገው የመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤት የረዳህ እንዴት ነው?

10 ደቂቃ፦ “jw.orgን በአገልግሎታችሁ ላይ ተጠቀሙበት—‘የይሖዋ ወዳጅ ሁን።’” በውይይት የሚቀርብ። በድረ ገጻችን ላይ የሚገኘው ይህ ክፍል ያሉትን አንዳንድ ገጽታዎች ጥቀስ፤ ከዚያም በዚህ ክፍል ውስጥ ካሉት ቪዲዮዎች አንዱን መርጠህ አጫውት። ወንድሞች “የይሖዋ ወዳጅ ሁን” የሚለውን ክፍል ከቤት ወደ ቤት፣ መንገድ ላይ ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሠክሩ እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 24 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ