ማስታወቂያዎች
◼ ጥር እና የካቲት፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት መጠቀም እንችላለን። ይህም ልጆችን ያጠቃልላል።) መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ በ2015 የአገልግሎት ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚሰጡት የሕዝብ ንግግር “የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነው” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።