“ለመልካም ሥራ የሚቀና” ሰው መሆን ያለብን ለምንድን ነው?
ለመልካም ሥራ ትቀናላችሁ? የመንግሥቱ ሰባኪዎች እንደመሆናችን መጠን ለመልካም ሥራ የምንቀናበት በቂ ምክንያት አለን። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? እስቲ በቲቶ 2:11-14 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች እንመርምር።
ቁጥር 11፦ “የአምላክ ጸጋ” ምንድን ነው? እኛስ ከአምላክ ጸጋ በግለሰብ ደረጃ ጥቅም ያገኘነው እንዴት ነው?—ሮም 3:23, 24
ቁጥር 12፦ የአምላክ ጸጋ ያሠለጠነን እንዴት ነው?
ቁጥር 13 እና 14፦ አሁን የነጻን ሰዎች በመሆናችን የትኛውን ተስፋ እንጠባበቃለን? በዚህ ዓለም ያሉ ፈሪሃ አምላክ የጎደላቸው ሰዎች ከሚፈጽሟቸው ድርጊቶች የነጻነው ለየትኛው ታላቅ ዓላማ ነው?
እነዚህ ጥቅሶች ለመልካም ሥራዎች ይበልጥ እንድትቀና ያነሳሱህ እንዴት ነው?