የካቲት 16 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 80 እና ጸሎት
bt ምዕ. 15 ከአን. 1-7 እና በገጽ 116 ላይ የሚገኘው የመግቢያ ሐሳብ (30 ደቂቃ)
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ መሳፍንት 15-18 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ መሳፍንት 16:13-24 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ምንድን ነው?—nwt-E ገጽ 12 አን. 1-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አጵሎስ—ጭብጥ፦ ትሑት፣ ጥሩ የመናገር ተሰጥኦ ያለውና ቀናተኛ ሰው—bt ገጽ 159 አን. 4-7 (5 ደቂቃ)
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ለመልካም ሥራ የምትቀኑ’ ሁኑ!—ቲቶ 2:14
15 ደቂቃ፦ ምሥራቹን በቅንዓት ለማወጅ ተዘጋጁ። በውይይት የሚቀርብ። ጸሎት ለአገልግሎት ለመዘጋጀት ልንወስደው የሚገባ የመጀመሪያ እርምጃ ነው የሚባለው ለምንድን ነው? (መዝ. 143:10፤ ሥራ 4:31) ጸሎት ከማቅረብ በተጨማሪ ምን ማድረግ ያስፈልጋል? (ዕዝራ 7:10 NW) ራሳችንን በመንፈሳዊ በደንብ ካዘጋጀን በኋላ ጽሑፎቻችንንና የአገልግሎት ቦርሳችንን ለማዘጋጀት ምን ማድረግ እንችላለን? ተዘጋጅተን መውጣታችን በእኛ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል? (የሐምሌ 15, 2008 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-10 አን. 9ን ተመልከት።) ለአገልግሎት የምትዘጋጀው እንዴት ነው? አንድ አስፋፊ በአገልግሎት ላይ ሊጠቀምበት ያሰበውን ትራክት፣ መጽሔት ወይም ብሮሹር ይዘት በመቃኘት ለአገልግሎት ሲዘጋጅ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በመቀጠል አስፋፊው የአገልግሎት ቦርሳውን ያዘጋጃል፤ እንዲሁም ቪዲዮ የሚያሳይበት መሣሪያ ቪዲዮ ለማጫወት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል። ሁላችንም አገልግሎት ከመውጣታችን በፊት በሚገባ መዘጋጀት እንዳለብን ጎላ አድርገህ ግለጽ። (2 ጢሞ. 3:17)
15 ደቂቃ፦ “በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የይሖዋና የኢየሱስ ዓይነት ቅንዓት ማሳየት ትችላላችሁ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት አንድ ቅጂ ለሁሉም እንዲታደል አድርግ፤ ከዚያም ስለ ይዘቱ ተናገር። በገጽ 4 ላይ የሚገኘውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም አንድ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 30 እና ጸሎት