የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 23, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
በጥንቷ እስራኤል የነበሩት የመማጸኛ ከተሞች ከአረማውያን የወንጀለኞች መደበቂያ የሚለዩት እንዴት ነው? (ኢያሱ 20:2, 3) [ጥር 5, w10 11/1 ገጽ 15 አን. 4-6]
ኢያሱ በኢያሱ 23:14 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በእርግጠኝነት ሊናገር የቻለው ለምንድን ነው? እኛስ ይሖዋ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ሙሉ በሙሉ ልንተማመን የምንችለው ለምንድን ነው? [ጥር 12, w07 11/1 ገጽ 26 አን 19]
ይሁዳ የተመደበለትን ርስት ከሌሎቹ ነገዶች ቀድሞ እንዲወስድ የተደረገው ለምንድን ነው? (መሳ. 1:2, 4) [ጥር 19, w05 1/15 ገጽ 24 አን. 5]
ባርቅ ነቢዪቱ ዲቦራ አብራው ወደ ጦር ሜዳ እንድትሄድ አጥብቆ የጠየቃት ለምንድን ነው? (መሳ. 4:8) [ጥር 19, w05 1/15 ገጽ 25 አን. 4]
ጌድዮን ለሠራው መሠዊያ የሰጠው ስያሜ ምን ያመለክታል? እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 6:23, 24) [ጥር 26, w14 2/15 ገጽ 22-23 አን. 9]
ጌድዮን ጠበኛ ለሆኑት ኤፍሬማውያን ከሰጠው ምላሽ ምን እንማራለን? (መሳ. 8:1-3) [የካ. 2, w05 7/15 ገጽ 16 አን. 4]
ዮፍታሔ ስእለት በተሳለበት ወቅት የሰው መሥዋዕት የማቅረብ ሐሳብ ነበረው? (መሳ. 11:30, 31) [የካ. 9, w05 1/15 ገጽ 26 አን. 1]
በመሳፍንት 11:35-37 መሠረት የዮፍታሔ ልጅ የአባቷን ስእለት እንድትጠብቅ ያደረጋት ምንድን ነው? [የካ. 9, w11 12/15 ገጽ 20-21 አን. 15-16]
በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ ‘እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን ማድረጉ’ ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግሥ አድርጎ ነበር? አብራራ። (መሳ. 17:6) [የካ. 16, w05 1/15 ገጽ 27 አን. 7
እስራኤላውያን አሳፋሪ ነገር ባደረጉት ብንያማውያን ሁለት ጊዜ እንደተሸነፉ ከሚገልጸው ዘገባ በጸሎት ስለ መጽናት ምን እንማራለን? (መሳ. 20:14-25) [የካ. 23, w11 9/15 ገጽ 32 ገጽ 1-4]