የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአሁኑ ወቅት በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ቢሮው የሚያደራጀው የአደባባይ ምሥክርነት በመሰጠት ላይ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ከተጠቀሱት በተጨማሪ በሐረር፣ በሐዋሳ፣ በሶዶ፣ በሻሸመኔ፣ በነቀምት፣ በአርባ ምንጭ፣ በዝዋይና በድሬዳዋ እንዲሁም በጅማ የአደባባይ ምሥክርነት በመሰጠት ላይ ይገኛል። በውጤቱም አስደሳች ሪፖርቶችን መስማት ችለናል። ለምሳሌ ያህል፣ በሐዋሳ በአንድ ቀን ብቻ ወደ 500 የሚጠጉ መጻሕፍትና ከ6,000 በላይ ትራክቶችን ማበርከት ችለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚገኙ አራት ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ የአደባባይ ምሥክርነት አደራጅተዋል፤ እንዲሁም ለዚህ ዓላማ የሚያገለግሉ ጋሪዎችንም ሆነ ጽሑፎችን አዘው አስመጥተዋል። ሌሎችም ጉባኤዎች እንዲሁ ያደርጋሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።