ሚያዝያ 20 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 17 ከአን. 15-19 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 23-25 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ሳሙኤል 23:13-23 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ ምን ተስፋ ይዟል?—nwt ገጽ 20 አን. 1-3 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ባሮክ—ጭብጥ፦ ይሖዋን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ማገልገል—w06 8/15 ገጽ 17 አን. 8 እስከ ገጽ 19 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ በመጠቀም’ እንደ ጥበበኛ ሰዎች ተመላለሱ።—ኤፌ. 5:15, 16
15 ደቂቃ፦ “በጽሑፍ መደርደሪያዎች ተጠቅሞ መመሥከር የሚቻለው እንዴት ነው?” በውይይት የሚቀርብ። የሚከተለው ሁኔታ በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ፦ ሁለት አስፋፊዎች የጽሑፍ ጋሪ ወይም ጠረጴዛ አጠገብ ቆመዋል። አንደኛው አስፋፊ በአጠገባቸው ለሚያልፍ ሰው ሞቅ ያለ ፈገግታ ያሳየዋል፤ ሰውየው ግን ዝም ብሎ ያልፋል። ከዚያም ሌላኛው አስፋፊ በዚያ ለሚያልፍ ሌላ ሰው ሞቅ ያለ ፈገግታ ያሳያል፤ ይሄኛው ግለሰብ ግን ወደ አስፋፊው ይቀርባል፤ በዚህ ጊዜ አስፋፊው ጥያቄ ይጠይቀውና ሞቅ ያለ ውይይት ይጀምራሉ። እንዲህ ዓይነቱን አቀራረብ በጽሑፍ መደርደሪያ ተጠቅመን ስናገለግል ብቻ ሳይሆን በሌሎች አጋጣሚዎችም ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?
15 ደቂቃ፦ ደስታ የሚያስገኙ ዓመታዊ ስብሰባዎች። በመስከረም 15, 2012 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 31 አንቀጽ 15 እስከ ገጽ 32 አንቀጽ 19 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ከፊታችን ላለው የክልል ስብሰባ አድናቆት እንዲያድርባቸው አድርግ። ሁሉም jw.org ላይ የወጣውን የስብሰባ ፕሮግራም እንዲመለከቱ በማበረታታት በስብሰባው ላይ የሚቀርቡትን ነገሮች በጉጉት እንዲጠብቁ አድርግ።
መዝሙር 75 እና ጸሎት