ግንቦት 4 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 68 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 18 ከአን. 6-11 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 1-3 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 2:24-32 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ 2፦ ቤርሳቤህ—ጭብጥ፦ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞች የአምላክን ሞገስ ማግኘት ይችላሉ—w07 7/15 ገጽ 19 አን. 13 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ በቅርቡ የሚፈጸሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ተስፋዎች—nwt ገጽ 20 አን. 4 እስከ ገጽ 21 አን. 1 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ በመጠቀም’ እንደ ጥበበኛ ሰዎች ተመላለሱ።—ኤፌ. 5:15, 16
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት። መጽሔት ለማበርከት የሚረዱ መግቢያዎችን በሠርቶ ማሳያ ማቅረብንም ሊያካትት ይቻላል።
5 ደቂቃ፦ በግንቦትና በሰኔ ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። የሚበረከተው ጽሑፍ ያሉትን አንዳንድ ገጽታዎች ተናገር። አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ እምብዛም ባልተሠራባቸው ክልሎች ውስጥ መስበክ—ጊዜያችንን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስችለን መንገድ! አንድ ሽማግሌ በውይይት የሚያቀርበው፤ እምብዛም ባልተሠራባቸው ክልሎች ውስጥ ያገለገለ ሽማግሌ ቢሆን ይመረጣል። ርቆ በሚገኝ አካባቢ መስበክ—አውስትራሊያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። (jw.org/am ውስጥ ስለ እኛ > እንቅስቃሴዎች በሚለው ሥር ይገኛል።) በቪዲዮው ላይ እንደታየው የቤተሰቡ አባላት እምብዛም ባልተሠራበት ክልል ውስጥ መስበካቸው ምን በጎ ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው ተወያዩ። በጉባኤው ውስጥ እምብዛም ባልተሠራባቸው ክልሎች ውስጥ ያገለገሉ አስፋፊዎች ካሉ ቃለ መጠየቅ አድርግላቸው። በቤተሰባቸው፣ በአገልግሎታቸውና በመንፈሳዊነታቸው ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል? ምን ዓይነት ዕቅድ ማውጣት አስፈልጓቸው ነበር? እምብዛም ባልተሠራባቸው ክልሎች ውስጥ ለማገልገል ፍላጎት ያለው አስፋፊ ካለ ሽማግሌዎች አስፈላጊውን እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው። እምብዛም ባልተሠራባቸው ክልሎች ውስጥ ማገልገል ጊዜያችንን በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችለን ግሩም አጋጣሚ እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ።
አዲስ መዝሙር፦ “ጸንተው እንዲቆሙ አስተምሯቸው” እና ጸሎት
ማሳሰቢያ፦ እባካችሁ መጀመሪያ ሙዚቃውን ብቻ አጫውቱ፤ ከዚያም ጉባኤው አዲሱን መዝሙር አብሮ ይዘምር።