የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 29, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
ሜልኮል ዳዊትን ያናገረችበት መንገድ ተገቢ አልነበረም የምንለው ለምንድን ነው? ባለትዳሮች ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? (2 ሳሙ. 6:20-23) [ግን. 11, w11 8/1 ገጽ 12 አን. 1]
ነቢዩ ናታን፣ ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንዲገነባ በመናገሩ ይሖዋ እርማት በሰጠው ወቅት ምን ምላሽ ሰጥቷል? (2 ሳሙ. 7:2, 3) [ግን. 11, w12 2/15 ገጽ 24 አን. 6-7]
ናታን፣ ዳዊት ከባድ ኃጢአት እንደሠራ በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በሁለተኛ ሳሙኤል 12:1-7 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ምሳሌ የተናገረው ለምንድን ነው? ይህ ዘገባ የማስተማር ችሎታችንን እንድናሻሽል የሚረዳን እንዴት ነው? [ግን. 18, w12 2/15 ገጽ 24 አን. 2-3]
አቢሴሎም እስራኤላውያንን ማታለል የቻለው ለምንድን ነው? እኛስ የዘመናችን “አቢሴሎሞች” እንዳያታልሉን ምን ማድረግ እንችላለን? (2 ሳሙ. 15:6) [ግን. 25, w12 7/15 ገጽ 13 አን. 7]
ዳዊት መሠረታዊ ነገሮችን በማጣት ችግር ላይ በወደቀበት ወቅት ይሖዋ የሚያስፈልገውን ነገር ያሟላለት እንዴት ነው? እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? (2 ሳሙ. 17:27-29) [ሰኔ 1, w08 9/15 ገጽ 5-6 አን. 15-16]
ዳዊት ኢታይ ከተባለ የባዕድ አገር ሰው ጋር የነበረው ግንኙነት ምን ያስተምረናል? (2 ሳሙ. 18:2) [ሰኔ 1, w09 5/15 ገጽ 27 አን. 7]
ቤርዜሊ በጉባኤ ውስጥ ላሉ በዕድሜ የገፉ ወንድሞችና እህቶች ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (2 ሳሙ. 19:33-35) [ሰኔ 8, w07 7/15 ገጽ 15 አን. 1-2]
ዳዊት ስለ ታማኝነት የተናገረው ሐሳብ በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የይሖዋ አገልጋዮችን የሚያበረታታው እንዴት ነው? (2 ሳሙ. 22:26) [ሰኔ 15, w10 6/1 ገጽ 26 አን. 6-7]
ናታን ለአምላክ ያለውን ታማኝነት ያሳየው እንዴት ነው? እኛስ ይህን ባሕርይ በማንጸባረቅ የእሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (1 ነገ. 1:11-14) [ሰኔ 22, w12 2/15 ገጽ 25 አን. 1, 4-5]
አንድ የአምላክ አገልጋይ ሰለሞን ካደረገው ነገር ጋር በሚመሳሰል መልኩ የአምላክን ትእዛዝ ላለመፈጸም ምን ዓይነት ሰበብ ሊያቀርብ ይችላል? (1 ነገ. 3:1) [ሰኔ 29, w11 12/15 ገጽ 10 አን. 12-14]