ሰኔ 15 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሰኔ 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 77 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 20 ከአን. 1-7 እና በገጽ 156 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ሳሙኤል 22-24 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ሳሙኤል 22:21-32 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ቃየን—ጭብጥ፦ ምክር ሲሰጠን የምናሳየው ምላሽ ስለ እኛ ማንነት ይናገራል—w08 10/15 ገጽ 5 አን. 10-11 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ፍቅርና ታዛዥነት ደስታ ያስገኛሉ—nwt ገጽ 26 አን. 4-6 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “የጥንቱን ዘመን አስታውስ።”—ዘዳ. 32:7
12 ደቂቃ፦ በጣም የምትወዱት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሰው ማን ነው? በቃለ መጠይቅና በንግግር የሚቀርብ። ክፍልህን በጉባኤ ውስጥ ላሉ ሁለት ወይም ሦስት ትናንሽ ልጆች ቃለ መጠይቅ በማድረግ ጀምር። በጣም የሚወዱት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሰው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህ ሰዎች ምን እንዳደረጉ ይናገራል? እነዚህን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎች መምሰል የሚፈልጉት በየትኞቹ መንገዶች ነው? ከዚያም ልጆች jw.org ላይ ከሚገኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ካርዶች ከሚለው ክፍል ጥቅም ማግኘት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ በንግግር አቅርብ። (የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ልጆች በሚለው ሥር ይገኛል) እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ካርድ የባለ ታሪኩን አጭር የሕይወት ታሪክ፣ ምስሉን፣ ይኖርበት የነበረውን ቦታ እንዲሁም ከእሱ ጋር የተያያዙ ሦስት ጥያቄና መልሶችን ይዟል። እያንዳንዱ ካርድ የተዘጋጀው ታትሞ ከሌሎቹ ጋር እንዲቀመጥ በሚያስችል መንገድ ነው። ትናንሽ ልጆች ያሏቸው ወላጆች “የጥንቱን ዘመን” ለልጆቻቸው ለማስተማር ይህን ገጽታ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት አበረታታ።—ዘዳ. 32:7
18 ደቂቃ፦ “የበለጠ ተሞክሮ ካላቸው አስፋፊዎች መማር” በውይይት የሚቀርብ። በአንቀጽ ሁለት ላይ ስትወያዩ ይበልጥ ልምድ ካላቸው አስፋፊዎች ጋር በማገልገላቸው የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 4 እና ጸሎት