ሐምሌ 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሐምሌ 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 22 ከአን. 1-6 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ነገሥት 15-17 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ነገሥት 15:16-24 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚስቶች ምን ጠቃሚ ምክር ይዟል?—nwt ገጽ 30 አን. 3-4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ ዳዊት—ጭብጥ፦ ወጣቶች፣ ይሖዋን በድፍረት ለማገልገል ከአሁኑ ተዘጋጁ—w11 9/1 ገጽ 26-29 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጉ።’—ማቴ. 28:19, 20
10 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችሁን እያዳበራችሁ ነው? በውይይት የሚቀርብ። “በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር” የሚለው ተከታታይ ርዕስ የሚወጣበትን ዓላማ በተመለከተ በየካቲት 2014 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከሚገኘው ክፍል የመጀመሪያውን አንቀጽ ከልስ። ከዚህ በፊት የወጡ አንዳንድ ርዕሶችን በአጭሩ ከልስ። አድማጮች ከዚህ ዓምድ ያገኙትን ጥቅም እንዲናገሩ ጋብዝ። አስፋፊዎች “በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር የሚወጡትን ሐሳቦች በዚያው ወር ተግባራዊ በማድረግ በወሩ ውስጥ ትኩረት ለተደረገበት ክህሎት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን ለመርዳት “ከአምላክ ቃል ጋር ተዋወቅ” የሚለውን ክፍል ተጠቀሙበት። በውይይት የሚቀርብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ እንዲጠቀሙበት ለመርዳት የሚከተሉት ገጽታዎች የሚረዱን እንዴት እንደሆነ አብራራ፦ (1) “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ማውጣት የሚቻልበት ዘዴ።” (2) ጥያቄ 19፦ “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጻሕፍት ምን ይዘዋል?” (3) ጥያቄ 20፦ “ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሻለ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?” አንድ አስፋፊ ጥናት አስጠንቶ ሊጨርስ ሲል ከላይ ከተጠቀሱት ገጽታዎች መካከል በአንዱ ላይ ከጥናቱ ጋር ውይይት ሲያደርግ የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ “ለማስተማር የምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 125 እና ጸሎት