የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በቅርንጫፍ ቢሯችን ሥር የሚገኙ አዳዲስና አልፎ አልፎ የሚሸፈኑ ክልሎች ውስጥ ለመስበክ የተደረገው የሦስት ወር ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ በመጋቢት ወር ተጠናቋል። በዚህ ዘመቻ ከተካፈሉት 376 ወንድሞችና እህቶች መካከል 15ቱ ከውጭ አገር የመጡ ናቸው። በዘመቻው በአጠቃላይ 139 ክልሎች የተሸፈኑ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 23ቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራባቸው ናቸው። በዚህ ዘመቻ ወቅት ጥሩ ምሥክርነት የተሰጠ ከመሆኑም ሌላ ብዙዎች የአገልግሎት መንፈሳቸው ተነቃቅቷል፤ ብዙ አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችም ተገኝተዋል። በዚህ ዘመቻ የተካፈሉ ወንድሞች ይህ አጋጣሚ ብዙ በረከት እንዳስገኘላቸው ተናግረዋል። ይሖዋ መንፈሳዊውን መከር የመሰብሰቡን ሥራ ‘እያፋጠነው’ ስለሆነ ራሳችንን በፈቃደኝነት ካቀረብን ልንሠራው የምንችለው ብዙ ሥራ አለ።—ኢሳ. 60:22