የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ መስከረም 1
“የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] የዚህን ጥያቄ መልስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ ስሙን በገለጸበት ቦታ ላይ እናገኛለን። [መዝሙር 83:18ን አንብብ።] የይሖዋ ምሥክሮች ስለሆንን ስለ እሱም ሆነ ለሰው ልጆች ስላለው ዓላማ ለሰዎች እናሳውቃለን። ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም የይሖዋ ምሥክሮችን በተመለከተ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ይረዳል።”
ንቁ! መስከረም
“ብዙ ሰዎች ለመኖር ገንዘብ ያስፈልጋል በሚለው ሐሳብ ይስማማሉ። ይሁንና ስለ ገንዘብ ከልክ በላይ መጨነቅ አደገኛ ነው ቢባል አይስማሙም? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ ልብ ይበሉ። [1 ጢሞቴዎስ 6:9ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት ማዳበር የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”