መስከረም 28 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 73 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 25 ከአን. 1-7፣ በገጽ 199 እና 200 ላይ የሚገኙት ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ነገሥት 23-25 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ነገሥት 23:8-15 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ መላእክት በአምላክ ዓላማ ውስጥ ምን ሚና አላቸው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ከገጽ 1625-1626 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አልዓዛር—ጭብጥ፦ ይሖዋን በድፍረት አገልግሉት—w98 12/15 ገጽ 12 አን. 13 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ መሥክሩ።’—ሥራ 20:24
10 ደቂቃ፦ ጳውሎስና የአገልግሎት ጓደኞቹ በፊልጵስዩስ የተሟላ ምሥክርነት ሰጡ። በውይይት የሚቀርብ። የሐዋርያት ሥራ 16:11-15 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
20 ደቂቃ፦ “ምሥራች በተባለው ብሮሹር ተጠቅሞ ማስጠናት።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 3 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ አንድ አስፋፊ ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክትና በአንድ አንቀጽ ላይ ሲወያይ የሚያሳይ ጥሩ ዝግጅት የተደረገበት ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 114 እና ጸሎት