ጥቅምት 19 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 19 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 54 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 26 ከአን. 1-8 እና በገጽ 204 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 8-11 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ዜና መዋዕል 11:15-25 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ኤልያስ—ጭብጥ፦ ጸሎት ያለውን ኃይል አቅልላችሁ አትመልከቱ—w08 1/1 ገጽ 19 አን. 4 እስከ ገጽ 21 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ የመላእክት አለቃ ማን ነው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ገጽ 1643 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “ሥር ሰዳችሁ” እና “በእምነት ጸንታችሁ” ኑሩ።—ቆላ. 2:6, 7
20 ደቂቃ፦ “የምናስተምራቸውን ሰዎች ልብ መንካት የምንችለው እንዴት ነው?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። ተቃራኒ ሁኔታዎችን የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። የቤቱ ባለቤት ልጇ እንደሞተና በአሁኑ ጊዜ በሰማይ እንደሚገኝ ትገልጻለች። በመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው መክብብ 9:5ን በማንበብ ሙታን ስለሚገኙበት ሁኔታ ይነግራታል። ሆኖም የቤቱ ባለቤት የተጠቀሰው ሐሳብ ስላላጽናናት ጥሩ ያልሆነ ምላሽ ትሰጣለች። በሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ አስፋፊው ዮሐንስ 5:28, 29ን ያነብና ርዕሰ ጉዳዩን በዘዴ ወደ ትንሣኤ ተስፋ ዞር እንዲል ያደርጋል፤ በዚህም ምክንያት ከቤቱ ባለቤት ጥሩ ምላሽ ያገኛል።
10 ደቂቃ፦ ወጣትም ሆናችሁ አረጋዊ ለሌሎች ጥሩ አርዓያ ሁኑ። (ፊልጵ. 3:17፤ 1 ጢሞ. 4:12) በ2015 የዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ከገጽ 71 አንቀጽ 2 እስከ ገጽ 72 አንቀጽ 4 እንዲሁም ከገጽ 76-77 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
መዝሙር 90 እና ጸሎት