ታኅሣሥ 7 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ታኅሣሥ 7 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 86 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 28 ከአን. 8-15 (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2 ዜና መዋዕል 10-14 (8 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 2 ዜና መዋዕል 13:13-22 (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አፍሮዲጡ—ጭብጥ፦ እምነት የሚጣልባቸውን የአምላክ አገልጋዮች አክብሩ—w10 6/15 ገጽ 12 አን. 10 እስከ ገጽ 13 አን. 12 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ “ቄሳር” የሚለው ቃል ምን ትርጉም አለው?—የቃላት መፍቻ፣ nwt ገጽ 1633 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “ወደ አምላክ መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን።”—ሥራ 14:22
10 ደቂቃ፦ “ወደ አምላክ መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን።” በወሩ ጭብጥ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። የሐዋርያት ሥራ 14:21, 22ን እና 1 ጴጥሮስ 4:12-14ን አንብብና አብራራ። (የመስከረም 15, 2014 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13 ከአንቀጽ 3-6ን ተመልከት።) በዚህ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡትን አንዳንድ ክፍሎች በአጭሩ ከልስ፤ እንዲሁም ከወሩ ጭብጥ ጋር ያላቸውን ተያያዥነት ግለጽ። በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚቀርበው ክፍል ‘በእምነት እንጂ በማየት አትመላለሱ’ የተባለውን ቪዲዮ ሁሉም አይተው እንዲመጡ አበረታታ።
10 ደቂቃ፦ ምን መልስ መስጠት ይኖርባችኋል? (ቆላ. 4:6) በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 69 ከአንቀጽ 1-3 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ተቃራኒ ሁኔታዎችን የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በመጀመሪያው ሠርቶ ማሳያ ላይ የቤቱ ባለቤት በቁጣ ሲናገረው አስፋፊውም በዚያው መንገድ አጸፋውን ይመልሳል፤ ይህም ውይይቱ በአሉታዊ ሁኔታ እንዲደመደም ያደርጋል። በሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ላይ ግን አስፋፊው፣ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥመው በተረጋጋ መንፈስ በመመለሱ የቤቱ ባለቤት አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል።
10 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ዕንባቆም።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 74 እና ጸሎት