ጥር 4-10
2 ዜና መዋዕል 29-32
መዝሙር 114 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“እውነተኛው አምልኮ ተግቶ መሥራት ይጠይቃል”፦ (10 ደቂቃ)
2ዜና 29:10-17—ሕዝቅያስ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ እውነተኛውን አምልኮ መልሶ አቋቋመ
2ዜና 30:5, 6, 10-12—ሕዝቅያስ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ለአምልኮ እንዲሰበሰቡ ጥሪ አስተላለፈ
2ዜና 32:25, 26—ሕዝቅያስ የትዕቢት ዝንባሌውን በትሕትና አስተካከለ (w05 10/15 25 አን. 20)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
2ዜና 29:11—ሕዝቅያስ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በማስቀደም ረገድ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (w13 11/15 17 አን. 6-7)
2ዜና 32:7, 8—ወደፊት ለሚያጋጥሙን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከወዲሁ ለመዘጋጀት ልንወስደው የምንችለው ከሁሉ የተሻለ እርምጃ ምንድን ነው? (w13 11/15 20 አን. 17)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 2ዜና 31:1-10 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች ተዘጋጅ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። የመጀመሪያውን የመጠበቂያ ግንብ የአቀራረብ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። አስፋፊው ለተመላልሶ መጠየቅ እንዴት መሠረት እንደጣለ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ከሁለተኛው የመጠበቂያ ግንብ የአቀራረብ ናሙና እና ምሥራች ከተባለው ብሮሹር የአቀራረብ ናሙና ጋር በተያያዘም ተመሳሳይ ነገር አድርግ። “ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ ጥናት መምራት የሚቻለው እንዴት ነው?” ከሚለው ርዕስ ላይ አንዳንድ ነጥቦችን ጥቀስ። አስፋፊዎች የራሳቸውን መግቢያ እንዲያዘጋጁ አበረታታ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“እውነተኛ አምልኮ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች መገንባትና በጥሩ ሁኔታ መያዝ”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። በመንግሥት አዳራሽ ግንባታ የተካፈሉ ወንድሞችና እህቶች ያገኙትን ደስታ እንዲናገሩ ጋብዝ። የመንግሥት አዳራሹን የጽዳትና የጥገና ሥራ የሚያስተባብረው ወንድም በዚህ ረገድ ጉባኤው ያደረጋቸውን ዝግጅቶች እንዲገልጽ ቃለ መጠይቅ አድርግለት።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ia ምዕ. 1 አን. 14-27፤ በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 142 እና ጸሎት
ማሳሰቢያ፦ እባካችሁ መጀመሪያ ሙዚቃውን ብቻ አጫውቱ፤ ከዚያ ጉባኤው አዲሱን መዝሙር አብሮ ይዘምር።