ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ልጆቻችሁ ክርስቶስን እንዲከተሉ አሠልጥኗቸው
ክርስቲያን ወላጆች ልጃቸው ‘ራሱን በመካድ የራሱን የመከራ እንጨት ተሸክሞ ኢየሱስን ሲከተል’ ከማየት የበለጠ የሚያስደስታቸው ነገር የለም። (ማር 8:34፤ 3ዮሐ 4) አንድ ወላጅ ልጁ ክርስቶስን እንዲከተል ማሠልጠን ማለትም ሕይወቱን ለይሖዋ እንዲወስንና እንዲጠመቅ መርዳት የሚችለው እንዴት ነው? አንድ ልጅ ለመጠመቅ ዝግጁ መሆኑን የሚጠቁሙ ምን ነገሮች ይኖራሉ?
የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ከገጽ 165-166 ላይ ያለውን “ለክርስቲያን ወላጆች” በሚለው ርዕስ ሥር የቀረበውን ሐሳብ አንብብና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦