ከኅዳር 12-18
የሐዋርያት ሥራ 1-3
መዝሙር 104 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“በክርስቲያን ጉባኤ ላይ መንፈስ ቅዱስ ፈሰሰ”፦ (10 ደቂቃ)
[የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ሥራ 2:1-8, 14, 37, 38, 41—የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ምሥራቹን ሰበኩ፤ በዚህም የተነሳ 3,000 የሚያህሉ ሰዎች ተጠመቁ
ሥራ 2:42-47—የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ታላቅ ልግስና እና የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ በማሳየታቸው፣ በቅርቡ የተጠመቁት አዲስ ደቀ መዛሙርት በኢየሩሳሌም በእንግድነት ቆይተው እምነታቸውን ማጠናከር ችለዋል (w86-E 12/1 29 አን. 4-5, 7)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሥራ 3:15—ኢየሱስ ‘የሕይወት ዋና ወኪል’ የተባለው ለምንድን ነው? (it-2-E 61 አን. 1)
ሥራ 3:19—ይህ ጥቅስ ይሖዋ ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር ስለሚልበት መንገድ ምን ያስተምረናል? (cl 265 አን. 14)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 2:1-21
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም።
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።
ንግግር፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) it-1-E 129 አን. 2-3—ጭብጥ፦ ይሁዳ በሌላ ሐዋርያ የተተካ ቢሆንም ታማኝ ሆነው የሞቱት ሐዋርያት በሌሎች ያልተተኩት ለምንድን ነው?
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“የተለያዩ ቋንቋዎች በሚነገሩበት ክልል ውስጥ ተባብረን መስበክ የምንችለው እንዴት ነው?”፦ (15 ደቂቃ) የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት። በጉባኤያችሁ ክልል ውስጥ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩ ከሆነ ከዚህ ጋር በተያያዘ ጉባኤው ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 35 አን. 20-27፣ “በመደጋገም ማስተማር” የሚለው ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 35 እና ጸሎት