ከኅዳር 19-25
የሐዋርያት ሥራ 4-5
መዝሙር 73 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“የአምላክን ቃል በድፍረት መናገራቸውን ቀጠሉ”፦ (10 ደቂቃ)
ሥራ 4:5-13—ጴጥሮስና ዮሐንስ “ያልተማሩና ተራ ሰዎች” ቢሆኑም የሚያምኑበትን ነገር ለገዢዎችና ለጸሐፍት ከመናገር ወደኋላ አላሉም (w08 9/1 15 ሣጥን፤ w08 5/15 31 አን. 1)
ሥራ 4:18-20—ጴጥሮስና ዮሐንስ ዛቻ ቢሰነዘርባቸውም መስበካቸውን አላቆሙም
ሥራ 4:23-31—በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ደፋሮች እንዲሆኑ የይሖዋ ቅዱስ መንፈስ ረድቷቸዋል (it-1-E 128 አን. 3)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሥራ 4:11—ኢየሱስ “የማዕዘን ራስ የሆነው ድንጋይ” የተባለው ለምንድን ነው? (it-1-E 514 አን. 4)
ሥራ 5:1—ሐናንያና ሰጲራ ከንብረታቸው የተወሰነውን የሸጡት ለምንድን ነው? (w13 3/1 15 አን. 3)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 5:27-42
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ግለሰቡ በክልላችሁ የተለመደ የተቃውሞ ሐሳብ ያነሳል።
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ግለሰቡ ክርስቲያን እንዳልሆነ ይናገራል።
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“በጋሪ የሚሰጥ ምሥክርነት በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ውጤት”፦ (15 ደቂቃ) የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። ቪዲዮውን አጫውት። ጉባኤያችሁ በጠረጴዛ ወይም በጋሪ በመጠቀም ምሥክርነት የሚሰጥ ከሆነ የጽሑፍ ጠረጴዛውን ወይም ጋሪውን ለአድማጮችህ አሳይ። ጉባኤው ከዚህ ጋር በተያያዘ ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ። ጊዜ ካለህ፣ በክልላችሁ የተገኘ ጥሩ ተሞክሮ ተናገር ወይም በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊዎች በዚህ የአገልግሎት መስክ መካፈል የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ግለጽ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 35 አን. 28-36
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 89 እና ጸሎት