ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 1 ቆሮንቶስ 10-13
ይሖዋ ታማኝ ነው
ይሖዋ ፈቃዱ ከሆነ ፈተናውን ሊያስወግደው ይችላል፤ ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ “መውጫ መንገዱን” የሚያዘጋጀው፣ ፈተናዎችን በጽናት መቋቋም እንድንችል የሚያስፈልገንን ድጋፍ በመስጠት ነው።
በቃሉ፣ በቅዱስ መንፈሱና በሚያቀርብልን መንፈሳዊ ምግብ አማካኝነት አእምሯችንን፣ ልባችንንና ስሜታችንን ያረጋጋልናል።—ማቴ 24:45፤ ዮሐ 14:16 ግርጌ፤ ሮም 15:4
በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ሊመራን ይችላል። መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎችንና መሠረታዊ ሥርዓቶችን እንድናስታውስ እንዲሁም መውሰድ የሚገባንን የጥበብ እርምጃ እንድናስተውል ይረዳናል።—ዮሐ 14:26
በመላእክቱ ተጠቅሞ ይረዳናል።—ዕብ 1:14
የእምነት አጋሮቻችንን በመጠቀም ይረዳናል።—ቆላ 4:11