ከግንቦት 27–ሰኔ 2
ገላትያ 1-3
መዝሙር 106 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ፊት ለፊት ተቃወምኩት”፦ (10 ደቂቃ)
[የገላትያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ገላ 2:11-13—አይሁዳዊ የሆኑ ክርስቲያኖች ሲመጡ ጴጥሮስ በሰው ፍርሃት ስለተሸነፈ ከአሕዛብ ወገን ከሆኑት ክርስቲያኖች ራሱን አገለለ (w17.04 27 አን. 16)
ገላ 2:14—ጳውሎስ ለጴጥሮስ እርማት ሰጠው (w13 3/15 5 አን. 12)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ገላ 2:20—ቤዛውን እንዴት ልትመለከተው ይገባል? ለምንስ? (w14 9/15 16 አን. 20-21)
ገላ 3:1—ጳውሎስ የገላትያ ሰዎችን “ማስተዋል የጎደላችሁ” ያላቸው ለምንድን ነው? (it-1 880)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ገላ 2:11-21 (th ጥናት 10)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። (th ጥናት 2)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (5 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs 202 አን. 18-19 (th ጥናት 6)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ረገድ ሁላችንም አስተዋጽኦ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?”፦ (15 ደቂቃ) አንድ ሽማግሌ በውይይት የሚያቀርበው። የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ የሚለውን ቪዲዮ ካጫወትክና በጥያቄዎቹ ላይ ከተወያያችሁ በኋላ በስብሰባ አዳራሽ ኮሚቴ ውስጥ ለሚገኘው የጉባኤያችሁ ተወካይ ቃለ መጠይቅ አድርግ። (በጉባኤያችሁ ውስጥ የስብሰባ አዳራሽ ኮሚቴ አባል ከሌለ ለሽማግሌዎች አካል አስተባባሪው ቃለ መጠይቅ አድርግ። በአዳራሻችሁ ውስጥ የሚሰበሰበው የእናንተ ጉባኤ ብቻ ከሆነ ለጥገና አስተባባሪው ቃለ መጠይቅ አድርግ።) የሚከተሉትን ጥያቄዎች አቅርብለት፦ አዳራሹን በጥሩ ሁኔታ ለመያዝ የወጣውን ፕሮግራም ተከትለን እየሠራን ነው? ሥራችንን ስናከናውን ከደህንነት ጋር የተያያዙ ጥንቃቄዎችን እናደርጋለን? በቅርብ ጊዜ ውስጥ የትኞቹ የጥገና ሥራዎች ተካሂደዋል? ለወደፊቱስ ምን ለመሥራት ታቅዷል? አንድ ሰው የጥገና ሙያ ካለው ወይም የጥገና ሙያ ካላቸው ጋር አብሮ በመሥራት የጥገና ክህሎት ማዳበር ከፈለገ ምን ማድረግ አለበት? ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ሁላችንም የስብሰባ አዳራሹን በጥሩ ሁኔታ ለመያዝ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት የምንችለው እንዴት ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 59
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 51 እና ጸሎት