ክርስቲያናዊ ሕይወት
የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ረገድ ሁላችንም አስተዋጽኦ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
የስብሰባ አዳራሾቻችን ለይሖዋ የተወሰኑ የአምልኮ ቦታዎች በመሆናቸው እንደ ማንኛውም ሕንፃ ልንቆጥራቸው አይገባም። የስብሰባ አዳራሻችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ረገድ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት የምንችለው እንዴት ነው?
የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የስብሰባ ቦታዎቻችን ለምን ዓላማ ያገለግላሉ?
የስብሰባ አዳራሻችንን በንጽሕናና በጥሩ ሁኔታ መያዝ ያለብን ለምንድን ነው?
የስብሰባ አዳራሻችንን በጥሩ ሁኔታ ለመያዝ በሚደረገው ጥረት በመካፈልህ የተጠቀምከው እንዴት ነው?
ከደህንነት ጋር የተያያዙ ጥንቃቄዎች ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ቪዲዮው ላይ ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ ምን ምሳሌዎች ተመልክተሃል?
መዋጮ በማድረግ ይሖዋን ማክበር የምንችለው እንዴት ነው?
የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማበርከት ምን ላደርግ አስቤያለሁ?