ክርስቲያናዊ ሕይወት
የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ
የመንግሥት አዳራሾቻችን ለይሖዋ የተወሰኑ የአምልኮ ቦታዎች በመሆናቸው ከሌሎች መሰብሰቢያዎች የተለዩ ናቸው። የመንግሥት አዳራሻችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት የምንችለው እንዴት ነው? የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ የተባለውን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ።
መንግሥት አዳራሾቻችን ለምን ዓላማ ያገለግላሉ?
የመንግሥት አዳራሹን በንጽሕናና በጥሩ ሁኔታ መያዝ ያለብን ለምንድን ነው?
የመንግሥት አዳራሹን ጥገና የመከታተል ኃላፊነት ያለበት ማን ነው?
ከደህንነት ጋር የተያያዙ ጥንቃቄዎች ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ቪዲዮው ላይ ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ ምን ምሳሌዎች ተመለከታችሁ?
መዋጮ በማድረግ ይሖዋን ማክበር የምንችለው እንዴት ነው?