የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ጥር ገጽ 9
  • ይሖዋ እና ኢየሱስ ወደፊት የሚያስገኙልን ነፃነት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ እና ኢየሱስ ወደፊት የሚያስገኙልን ነፃነት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ፈተናዎችን እንድንወጣ ይረዳናል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ለፈተናዎች ሊኖረን የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ጽናት
    ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ጥር ገጽ 9
ኢየሱስ በሰማይ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ወደ ታች ሲመለከት፤ ከይሖዋ ዙፋን የሚወጣው ነጸብራቅ ከኋላው ይታያል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ እና ኢየሱስ ወደፊት የሚያስገኙልን ነፃነት

በየዕለቱ ከየትኞቹ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ጋር ትታገላለህ? ብዙ ኃላፊነቶች የተደራረቡብህ የቤተሰብ ራስ ነህ? ልጆችሽን ለማሳደግ ደፋ ቀና የምትዪ ነጠላ እናት ነሽ? እኩዮችህ የሚያስቸግሩህ ተማሪ ነህ? የጤና እክል ወይም የዕድሜ መግፋት ከሚያስከትላቸው ችግሮች ጋር እየታገልክ ነው? ሁላችንም የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። በርካታ ክርስቲያኖች ደግሞ ብዙ ችግሮች በላይ በላይ ተደራርበውባቸዋል። ሆኖም በቅርቡ ከእነዚህ ችግሮች እንደምንላቀቅ እናውቃለን።—2ቆሮ 4:16-18

እስከዚያው ድረስ ግን ይሖዋ የምናደርገውን ትግል እንደሚረዳልን፣ ታማኝነታችንንና ጽናታችንን እንደሚያደንቅ እንዲሁም ታላቅ በረከት እንዳዘጋጀልን ማወቃችን ያጽናናናል። (ኤር 29:11, 12) ኢየሱስም በግለሰብ ደረጃ ያስብልናል። ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን ስንወጣ ‘ከእኛ ጋር እንደሚሆን’ ቃል ገብቶልናል። (ማቴ 28:20) በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ስለምናገኘው ነፃነት ስናሰላስል ተስፋችን ይበልጥ እውን ሆኖ ይታየናል፤ እንዲሁም የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም ያለን ቁርጠኝነት ይጠናከራል።—ሮም 8:19-21

አውሎ ነፋሱ ሲቃረብ ኢየሱስን በትኩረት ተመልከቱ!—መንግሥቱ የሚያስገኛቸው በረከቶች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የሰው ልጆች ከአምላክ የራቁት እንዴት ነው? ውጤቱስ ምን ሆነ?

  • ለአምላክ ታማኝ የሆኑ ሰዎች ምን ተስፋ ይጠብቃቸዋል?

  • የሰው ልጆች ይህ አስደናቂ ተስፋ ሊኖራቸው የቻለው እንዴት ነው?

  • በአዲሱ ዓለም ውስጥ አንተ ለማግኘት የምትጓጓው የትኞቹን በረከቶች ነው?

ምስሎች፦ ሰዎች ገነት ውስጥ ተደስተው ሲኖሩ። 1. አንዲት እህት ትንሣኤ ያገኘችን ሴት ስታቅፍ። 2. ምግብ ተትረፍርፎ፣ ምድር ንጹሕ ሆና እንዲሁም ሰላም ሰፍኖ።

በአዲሱ ዓለም ውስጥ ስትኖር ይታይህ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ