የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 መጋቢት ገጽ 9
  • ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታማኝነት የሚያስከትለውን ፈተና መቋቋም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • “አንተ ብቻ ታማኝ ነህ”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • ከይሖዋ ድርጅት ጋር በታማኝነት ማገልገል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ታማኝ የሆኑትን ተመልከቱ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 መጋቢት ገጽ 9
ምድሪቱ አፏን ከፍታ ዓመፀኞቹን እስራኤላውያን ስትውጣቸው።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ

ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን በይሖዋ ዝግጅት ላይ በማመፅ ለእሱ ታማኝ አለመሆናቸውን አሳይተዋል። ይሖዋ ዓመፀኞቹንና ተባባሪዎቻቸውን በሙሉ አጥፍቷቸዋል። (ዘኁ 16:26, 27, 31-33) እኛስ ለይሖዋ ያለንን ታማኝነት የሚፈትን ምን ሁኔታ ሊያጋጥመን ይችላል? ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን እንዳንመስል የሚረዱን የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ናቸው?

ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ናዲያ መረን በለቀቀ ግብዣ ላይ አንድ ልጅ የአልኮል መጠጥ ሲሰጣት በዓይነ ሕሊናዋ ስታይ።

    ናዲያ ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሟታል? ታማኝ እንድትሆን የረዳትስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • ‘ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። አንድ የተበሳጨ ወንድም ስላሳሰበው ጉዳይ ሲያስብ።

    ተገቢ ያልሆነ ነገር እንደተፈጸመ የተሰማው አንድ ወንድም የተፈተነው እንዴት ነው? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • ‘ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ቴረንስ ከባሏ ከተፋታች አንዲት እህት ጋር ብቻውን በስብሰባ አዳራሹ የመኪና ማቆሚያ ላይ ሲነጋገር በዓይነ ሕሊናው ሲያይ።

    ቴረንስ ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

  • ‘ታማኝ ያልሆኑ ሰዎችን አትምሰሉ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ወንድም ወደ ስልኩ የተላከለትን የኢንተርኔት ቁማር መጫወቻ ድረ ገጽ ሊንክ ሲያይ።

    አንድ ወንድም በትምህርት ቤት ምን ፈታኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? ታማኝ እንዲሆን የረዳውስ የትኛው የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ