የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ ግንቦት-ሰኔ 2021
ከግንቦት 3-9
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘኁልቁ 27–29
“የማያዳላውን ይሖዋን ምሰሉ”
ስለ ይሖዋ ባሕርያት የተሟላ ግንዛቤ ይኑራችሁ
14 አምስቱ እህትማማቾች ወደ ሙሴ ቀርበው “አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት [ይሰጠን]” አሉ። በዚህ ጊዜ ሙሴ ‘እንግዲህ መመሪያው አንድ ነው፤ ምንም ልረዳችሁ አልችልም’ አላቸው? በፍጹም፤ ከዚህ ይልቅ “ጕዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ።” (ዘኍ. 27:2-5) ታዲያ ይሖዋ ምን ምላሽ ሰጠ? ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በእርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።” ይሖዋ እንዲህ ዓይነት መመሪያ በመስጠት ብቻ አልተወሰነም። ይህ አሠራር ለሰለጰዓድ ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም እስራኤላውያን የሚያገለግል ደንብ እንዲሆን ሲል “አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ” የሚል መመሪያ ለሙሴ ሰጠው። (ዘኍ. 27:6-8፤ ኢያሱ 17:1-6) ከዚያ በኋላ እንደ ሰለጰዓድ ልጆች ያለ ሁኔታ የሚያጋጥማቸው እስራኤላውያን ሴቶች በሙሉ ከዚህ ዝግጅት ጥቅም ማግኘት ይችላሉ።
ስለ ይሖዋ ባሕርያት የተሟላ ግንዛቤ ይኑራችሁ
15 ይህ እንዴት ያለ ደግነት የተንጸባረቀበትና ከአድልዎ ነፃ የሆነ ውሳኔ ነው! ይሖዋ የተሻለ ሁኔታ ለነበራቸው ሌሎች እስራኤላውያን እንደሚያደርገው ሁሉ ከጎናቸው የሚሆን ረዳት የሌላቸውን እነዚህን ሴቶችም በአክብሮት ይዟቸዋል። (መዝ. 68:5) ይሖዋ ያለውን አስደሳች ባሕርይ ይኸውም ሁሉንም አገልጋዮቹን ከአድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ የሚይዝ መሆኑን ከሚያሳዩ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ይህ አንዱ ብቻ ነው።—1 ሳሙ. 16:1-13፤ ሥራ 10:30-35, 44-48
ስለ ይሖዋ ባሕርያት የተሟላ ግንዛቤ ይኑራችሁ
16 የማያዳሉ በመሆን ረገድ ይሖዋን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው? የማያዳሉ መሆን ሁለት ነገሮችን እንደሚያካትት አስታውስ። ሌሎችን ከአድልዎ ነፃ በሆነ መንገድ መያዝ የምንችለው አመለካከታችን ከአድልዎ ነፃ ከሆነ ብቻ ነው። ማንኛችንም ብንሆን ሁሉንም ሰው እኩል እንደምንመለከትና እንደማናዳላ እናስብ ይሆናል። ይሁንና ብዙውን ጊዜ ራሳችንን በሐቀኝነት መመርመር እንደሚከብደን የታወቀ ነው። ታዲያ በዚህ ረገድ ምን ዓይነት ስም እንዳለን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? ኢየሱስ ሰዎች ስለ እሱ ምን እንደሚሉ ለማወቅ በፈለገ ጊዜ የሚያምናቸውን ወዳጆቹን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይሉታል?” በማለት ጠይቋቸው ነበር። (ማቴ. 16:13, 14) አንተም ለምን እንዲህ አታደርግም? ያሉብህን ድክመቶች በሐቀኝነት ወደሚነግርህ አንድ ወዳጅህ ቀርበህ በዚህ ረገድ ማሻሻል ያለብህ ነገር እንዳለ ልትጠይቀው ትችላለህ። የአንድን ሰው ዘር፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ቦታ ወይም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታውን አይተህ አድልዎ የማድረግ አዝማሚያ እንዳለህ ወዳጅህ ከጠቆመህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? አመለካከትህን ማስተካከልና እንደ እሱ ሙሉ በሙሉ ከአድልዎ ነፃ መሆን እንድትችል እንዲረዳህ ይሖዋን በጸሎት ተማጸነው።—ማቴ. 7:7፤ ቆላ. 3:10, 11
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-2 528 አን. 5
መባዎች
የመጠጥ መባዎች። የመጠጥ መባ ከሌሎች መባዎች ጋር የሚቀርብ መባ ነው፤ እስራኤላውያን ይህን መባ ማቅረብ የጀመሩት በተለይ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ ነው። (ዘኁ 15:2, 5, 8-10) ይህ መባ፣ የወይን ጠጅ (‘የሚያሰክር መጠጥ’) ሲሆን መሠዊያው ላይ ይፈስ ነበር። (ዘኁ 28:7, 14፤ ከዘፀ 30:9፤ ዘኁ 15:10 ጋር አወዳድር።) ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ላሉ ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል ጽፎላቸው ነበር፦ “በእምነት ተነሳስታችሁ በምታቀርቡት መሥዋዕትና ቅዱስ አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ መባ ብፈስ እንኳ ደስ ይለኛል።” እዚህ ላይ ጳውሎስ፣ የመጠጥ መባን እንደ ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመው ለእምነት ባልንጀሮቹ ሲል ራሱን ለመስጠት ያለውን ፈቃደኝነት ለመግለጽ ነው። (ፊልጵ 2:17) ከመሞቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ለጢሞቴዎስ “እኔ እንደ መጠጥ መባ እየፈሰስኩ ነውና፤ ደግሞም ነፃ የምለቀቅበት ጊዜ በጣም ቀርቧል” ሲል ጽፎለታል።—2ጢሞ 4:6
ከግንቦት 10-16
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘኁልቁ 30–31
“ስእለታችሁን ፈጽሙ”
it-2 1162
ስእለት
አንድ ሰው በፈቃደኝነት የሚያደርገው ነው፤ ከተሳለ በኋላ ግን ግዴታ ውስጥ ይገባል። ስእለት፣ አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ በራሱ ፈቃደኝነት የሚገባው ቃል ነው። አንዴ ከተሳለ ግን ስእለቱን የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት የአምላክ ሕግ ይናገራል። የሚሳለው ሰው ‘ነፍሱን ግዴታ ውስጥ እንደሚያስገባ’ የተገለጸው ለዚህ ነው፤ ይህ አባባል፣ ቃሉን እንደሚፈጽም የገዛ ሕይወቱን ዋስትና አድርጎ እንደሚሰጥ የሚጠቁም ነው። (ዘኁ 30:2፤ በተጨማሪም ሮም 1:31, 32ን ተመልከት) ጉዳዩ የሕይወት ጉዳይ ከመሆኑ አንጻር ቅዱሳን መጻሕፍት፣ አንድ ሰው ስእለት ከመሳሉ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰባቸው ተገቢ ነው፤ ግለሰቡ ስእለቱ ምን ግዴታ እንደሚያስከትልበት በጥሞና ማጤን ይኖርበታል። ሕጉ እንዲህ ይላል፦ “ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ . . . አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል። ሳትሳል ከቀረህ ግን ኃጢአት አይሆንብህም።”—ዘዳ 23:21, 22
it-2 1162
ስእለት
አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ፣ መባ ወይም ስጦታ ለመስጠት፣ አንድ ዓይነት አገልግሎት ለማከናወን ወይም ሕጉ የሚከለክላቸው ባይሆኑም ከአንዳንድ ነገሮች ለመታቀብ ለአምላክ የሚገባው ቃል ነው። ስእለት፣ አንድ ሰው በገዛ ፈቃዱ የሚገባው ቃል ነው። ስእለት ትልቅ ክብደት ሊሰጠው የሚገባ ቃል ነው፤ የመሐላን ያህል ክብደት ያለው ነገር ስለሆነ ሁለቱ አገላለጾች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብረው የሚጠቀሱበት ጊዜ አለ። (ዘኁ 30:2፤ ማቴ 5:33) “ስእለት” በዋነኝነት የሚያመለክተው አንድ ሰው ‘እንዲህ አደርጋለሁ’ ብሎ የሚገባውን ቃል ነው፤ “መሐላ” ደግሞ ቃል የተገባው ነገር እውነተኛ መሆኑን ወይም ተፈጻሚነቱን ለማረጋገጥ ከፍ ያለ ሥልጣን ያለውን አካል ጠርቶ መማልን የሚያመለክት ነው። ብዙውን ጊዜ ቃል ኪዳን የሚጸናው በመሐላ ነው።—ዘፍ 26:28፤ 31:44, 53
የዘኍልቍ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
30:6-8—አንድ ክርስቲያን ባል የሚስቱን ስዕለት ማስቀረት ይችላል? በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ሕዝቦቹ የሚያደርጉትን ስዕለት የሚመለከተው በግለሰብ ደረጃ ነው። ለአብነት ያህል፣ ራስን ለይሖዋ መወሰን አንድ ሰው በግሉ የሚያደርገው ስዕለት ነው። (ገላትያ 6:5) አንድ ባል እንዲህ ያለውን ስዕለት የማስቀረት ሥልጣን የለውም። ሚስትም ብትሆን ከአምላክ ቃል ወይም ለባሏ ካለባት ኃላፊነት ጋር የሚጋጭ ስዕለት ማድረግ አይኖርባትም።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-2 28 አን. 1
ዮፍታሔ
አንድ ሰው ከመቅደሱ ጋር በተያያዘ ሕይወቱን በሙሉ ለይሖዋ ቅዱስ አገልግሎት እንዲያቀርብ ሊሰጥ ይችላል። እንዲህ የማድረግ መብት ያላቸው ወላጆች ናቸው። ለእንዲህ ዓይነቱ አገልግሎት ከተሰጡት ልጆች አንዱ ሳሙኤል ነው፤ ገና ከመወለዱ በፊት እናቱ ሐና፣ ለማደሪያ ድንኳኑ አገልግሎት እንደምትሰጠው ተስላ ነበር። ባሏ ሕልቃናም ስእለቷን አልተቃወመም። ሳሙኤል ጡት እንደጣለ ሐና በመቅደሱ እንዲያገለግል ሰጠችው። ሐና ሳሙኤልን ወደ መቅደሱ ስትወስደው የእንስሳ መሥዋዕትም ይዛ ሄዳለች። (1ሳሙ 1:11, 22-28፤ 2:11) ሌላው ልጅ ደግሞ ሳምሶን ነው፤ ሳምሶን ናዝራዊ ሆኖ አምላክን እንዲያገለግል ተሰጥቷል።—መሳ 13:2-5, 11-14፤ በዘኁ 30:3-5, 16 ላይ ከተጠቀሰው አባት በሴት ልጁ ላይ ካለው ሥልጣን ጋር አወዳድር።
ከግንቦት 17-23
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘኁልቁ 32–33
“የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው”
ይህን ያውቁ ኖሯል?
በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ብዙ ጊዜ የተጠቀሱት ‘በኰረብታ ላይ የተሠሩ መስገጃዎች’ ወይም “የማምለኪያ ኰረብቶች” ምንድን ናቸው?
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በተቃረቡበት ጊዜ ይሖዋ በዚያ ይኖሩ የነበሩትን የከነዓናውያንን የማምለኪያ ቦታዎች በሙሉ እንዲያስወግዱ ነግሯቸው ነበር። አምላክ “የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ” በማለት አዟቸው ነበር። (ዘኍልቁ 33:52) እነዚህ የሐሰት አምልኮ ማዕከሎች በኮረብታ አናት ላይ የሚገኙ ምንም ዓይነት መጠለያ የሌላቸው ቦታዎች አሊያም በዛፎች ሥር ወይም በከተሞች ውስጥ እንደሚሠሩ ያሉ መድረኮች ሊሆኑ ይችላሉ። (1 ነገሥት 14:23፤ 2 ነገሥት 17:29፤ ሕዝቅኤል 6:3) እነዚህ ቦታዎች መሠዊያዎች፣ ቅዱስ ዓምዶች ወይም ምሰሶዎች፣ ምስሎች፣ የዕጣን ማጨሻዎችና ለአምልኮ የሚያገለግሉ ሌሎች ዕቃዎች ሊኖሯቸው ይችላሉ።
እስራኤላውያን ከፈጸሙት ስሕተት ትምህርት ማግኘት
በዛሬው ጊዜም እስራኤላውያን ያጋጠሟቸው ዓይነት በርካታ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ይገጥሙናል። በዘመናችን ያለው ኅብረተሰብ እንደ አምላክ የሚያያቸው በርካታ ነገሮች አሉ። ከእነዚህ መካከል ገንዘብ፣ የመዝናኛው ዓለም ኮከቦች፣ ታዋቂ ስፖርተኞች፣ የፖለቲካ ሥርዓቶች፣ አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎችና ሌላው ቀርቶ የቤተሰብ አባላት ይገኙበታል። ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱ በሕይወታችን ውስጥ ትልቁን ቦታ ሊይዝ ይችላል። ይሖዋን ከማይወዱ ሰዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት መመሥረት ለመንፈሳዊ ውድቀት ይዳርጋል።
ልቅ የሆነ የጾታ ብልግና እስራኤላውያንን የማረካቸውና ያሳታቸው የበዓል አምልኮ ዋነኛ ክፍል ነበር። ዛሬም ከአምላክ ሕዝቦች መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ ጋር በሚመሳሰሉ ወጥመዶች ተይዘዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ብቻውን ሆኖ ኢንተርኔት የሚመለከት ከፍተኛ የማወቅ ጉጉት ያለው ወይም ጥንቁቅ ያልሆነ አንድ ሰው፣ ጥቂት የኮምፒውተር ቁልፎችን በመጫን ብቻ ንጹሕ ሕሊናውን የሚያቆሽሹ ነገሮችን ሊመለከት ይችላል። አንድ ክርስቲያን በኢንተርኔት አማካኝነት የብልግና ሥዕሎችን በመመልከት ወጥመድ ውስጥ ቢወድቅ ምንኛ ያሳዝናል!
it-1 404 አን. 2
ከነአን
ኢያሱ ከነአናውያንን ከማጥፋት ጋር በተያያዘ “ይሖዋ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ሳይፈጽም የቀረው አንድም ነገር አልነበረም”፤ እንዲህ ማድረጉ የጥበብ እርምጃ ነበር። (ኢያሱ 11:15) እስራኤላውያን ግን በብሔር ደረጃ እሱ በዚህ ረገድ የተወውን ጥሩ ምሳሌ አልተከተሉም፤ ምድሪቱን ሊበክሉ የሚችሉ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ አላስወገዱም። እስራኤላውያን፣ ከነአናውያን ከእነሱ ጋር እንዲኖሩ መፍቀዳቸው ብሔሩ እንዲበከል አድርጓል፤ ይህ ደግሞ እስራኤላውያን በታዘዙት መሠረት ከነአናውያንን ከምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ቢያስወግዱ ኖሮ ከሚሞተው ሰው የበለጠ ብዙ ሰው እንዲሞት ምክንያት እንደሆነ ጥርጥር የለውም፤ ይህ እንግዲህ ወንጀሉን፣ የሥነ ምግባር ብልግናውንና ጣዖት አምልኮውን ሳይጨምር ነው። (ዘኁ 33:55, 56፤ መሳ 2:1-3, 11-23፤ መዝ 106:34-43) ይሖዋ የፍትሕና የፍርድ እርምጃ የሚወስደው ለየትኛውም ብሔር ሳያዳላ እንደሆነ እስራኤላውያንን በግልጽ አስጠንቅቋቸው ነበር፤ ከከነአናውያን ጋር ግንኙነት ከፈጠሩ፣ ከእነሱ ጋር ከተጋቡ፣ እምነታቸውን ከቀላቀሉ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ሥርዓቶቻቸውንና ርኩስ ልማዶቻቸውን ከተቀበሉ በከነአናውያኑ ላይ ያስተላለፈው የጥፋት ፍርድ በእነሱም ላይ እንደሚፈጸም አስጠንቅቋቸዋል፤ ‘ምድሪቱ እነሱንም እንደምትተፋቸው’ ነግሯቸዋል።—ዘፀ 23:32, 33፤ 34:12-17፤ ዘሌ 18:26-30፤ ዘዳ 7:2-5, 25, 26
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-1 359 አን. 2
ወሰን
በመጀመሪያ አንድ ነገድ የት ቦታ መስፈር እንዳለበት በዕጣ ይወሰናል፤ ከዚያም ርስቱ ምን ያህል ስፋት እንደሚኖረው አመጣጥኖ ማከፋፈል ያስፈልጋል። “ምድሪቱንም በየቤተሰባችሁ ውርስ አድርጋችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ተለቅ ላለው ቡድን በዛ ያለውን፣ አነስ ላለው ቡድን ደግሞ አነስ ያለውን ውርስ አድርጋችሁ ስጡት። ሁሉም በወጣለት ዕጣ መሠረት የተሰጠውን ቦታ ይወርሳል።” (ዘኁ 33:54) ነገዱ በዕጣ የደረሰው ቦታ ይጸናል፤ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችለው፣ ርስቱ በሚኖረው ስፋት ላይ ብቻ ነው። በመሆኑም የይሁዳ ነገድ የደረሰው ቦታ በጣም እንደበዛ ሲታወቅ ከርስቱ ላይ ተቀንሶ ለስምዖን ነገድ ተሰጥቷል።—ኢያሱ 19:9
ከግንቦት 24-30
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘኁልቁ 34–36
“ይሖዋን መሸሸጊያችሁ አድርጉት”
ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጋችሁታል?
4 ይሁንና በእስራኤል ውስጥ አንድ ሰው ሳያስበው ነፍስ ቢያጠፋ ምን ይደረግ ነበር? ግለሰቡ አውቆ ባይሆንም እንኳ ንጹሕ ደም አፍስሷል፤ በመሆኑም ከተጠያቂነት አያመልጥም። (ዘፍ. 9:5) ሆኖም እንዲህ ያለው ግለሰብ፣ ደም ተበቃዩ እንዳይገድለው ከስድስቱ የመማጸኛ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ ይችል ነበር፤ ይህም ምሕረት የተንጸባረቀበት ዝግጅት ነው። በዚያ ከተማ ውስጥ እንዲቆይ እስከተፈቀደለት ድረስ ጥበቃ ያገኛል። ሳያውቅ ነፍስ ያጠፋው ግለሰብ፣ ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛ ከተማ ውስጥ መቆየት ይገባዋል።—ዘኁ. 35:15, 28
ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጋችሁታል?
6 ሳያስበው ነፍስ ያጠፋው ግለሰብ፣ ከመማጸኛ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ በከተማዋ በር ላይ ቆሞ መጀመሪያ “ለከተማዋ ሽማግሌዎች ጉዳዩን [መናገር]” አለበት። ሽማግሌዎቹም ወደ ከተማቸው ያስገቡታል። (ኢያሱ 20:4) ከተወሰነ ጊዜ በኋላ፣ ይህ ግለሰብ የሰው ነፍስ ወዳጠፋበት ከተማ እንዲመለስና የዚያ ከተማ ሽማግሌዎች በጉዳዩ ላይ ፍርድ እንዲሰጡ ይደረጋል። (ዘኁልቁ 35:24, 25ን አንብብ።) ግለሰቡ ወደ መማጸኛ ከተማ እንዲመለስ የሚፈቀድለት ሽማግሌዎቹ፣ ነፍስ ያጠፋው ሳያስበው መሆኑን ከፈረዱ ብቻ ነው።
ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጋችሁታል?
13 ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ የሄደው ግለሰብ እዚያ ከደረሰ በኋላ ያለስጋት መኖር ይችላል። ይሖዋ ስለ እነዚያ ከተሞች ሲናገር “መሸሸጊያ ሆነው ያገለግሏችኋል” ብሏል። (ኢያሱ 20:2, 3) ይሖዋ፣ ነፍስ ያጠፋው ግለሰብ በዚያ ጉዳይ እንደገና ለፍርድ ሊቀርብ እንደሚችል የሚጠቁም ነገር አልተናገረም፤ ደም ተበቃዩም ቢሆን ወደ መማጸኛው ከተማ ገብቶ፣ ሳያውቅ ነፍስ ያጠፋውን ግለሰብ እንዲገድለው አይፈቀድለትም። በመሆኑም ሸሽቶ የሄደው ሰው፣ የበቀል እርምጃ ይወሰድብኛል ብሎ አይፈራም። በዚያ ከተማ ውስጥ እስካለ ድረስ ይሖዋ ጥበቃ ስለሚያደርግለት ያለስጋት መኖር ይችላል። የመማጸኛ ከተማ እስር ቤት አይደለም። በከተማዋ ውስጥ ሆኖ መሥራት፣ ሌሎችን መርዳት እንዲሁም ይሖዋን በሰላም ማገልገል ይችላል። በእርግጥም አስደሳችና የሚያረካ ሕይወት መምራት ይችላል!
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ለሁሉ የሚሆን ተመጣጣኝ ቤዛ
13 ይሁን እንጂ አዳምም ሆነ ሔዋን ከቤዛው ምንም ዓይነት ጥቅም አያገኙም። የሙሴ ሕግ የሚከተለውን መሠረታዊ ሥርዓት ይጨምር ነበር፦ “ሞት የተፈረደበትን ነፍሰ ገዳዩንም ለማዳን የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፤ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።” (ዘኁልቅ 35:31) አዳም አልተታለለም፤ ስለዚህ ኃጢአቱ ሆን ብሎ በፈቃደኝነት የፈጸመው ነበር። (1 ጢሞቴዎስ 2:14) ተወላጆቹ በሙሉ አለፍጽምና ስለወረሱና በዚህም ምክንያት የሞት ፍርድ ስለመጣባቸው ልጆቹን እንደገደላቸው ይቆጠራል። አዳም ፍጹም ሰው ሆኖ ሳለ የአምላክን ሕግ ለመጣስ ሆን ብሎ ስለመረጠ መሞት ይገባው እንደነበረ ግልጽ ነው። ይሖዋ አዳምን የቤዛው ተጠቃሚ ቢያደርገው የራሱን የጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓት መጣስ ይሆንበታል። የአዳም ኃጢአት ደመወዝ ቢከፈል ግን በአዳም ተወላጆች ላይ የተበየነው የሞት ፍርድ የሚወገድበትን መንገድ ያሰናዳል። (ሮሜ 5:16) ከሕግ አንጻር ስንመለከተው የኃጢአት የአጥፊነት ኃይል ከሥሩ ይቆረጣል ማለት ነው። ቤዛ የሚሆነው ሰው ’ለእያንዳንዱ ሰው ሞትን ይቀምሳል።’ ኃጢአት በአዳም ልጆች ላይ ያስከተለውን ጠንቅ በሙሉ ይሸከማል።—ዕብራውያን 2:9፤ 2 ቆሮንቶስ 5:21፤ 1 ጴጥሮስ 2:24
ከግንቦት 31–ሰኔ 6
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘዳግም 1–2
“‘ፍርድ የአምላክ ነው’”
ይሖዋ ጽድቅንና ፍትሕን ይወድዳል
ከባድ ኃጢአቶች በሚፈጸሙበት ወቅት የተሾሙ የጉባኤ ሽማግሌዎች ፍርድ የመስጠት ግዴታ አለባቸው። (1 ቆሮንቶስ 5:12, 13) ይህን በሚያደርጉበት ወቅት የአምላክ ፍትሕ በተቻለ መጠን ምሕረት ማድረግን እንደሚጠይቅ ያስታውሳሉ። ሆኖም ይህን ለማድረግ የሚያበቃ ምክንያት ከሌለ ማለትም ኃጢአት የሠራው ግለሰብ ንስሐ የማይገባ ከሆነ ምሕረት ሊደረግ አይችልም። ይሁን እንጂ ሽማግሌዎች እንደዚህ ያለውን ኃጢአተኛ ከጉባኤ የሚያስወግዱት ለመበቀል ብለው አይደለም። የውገዳ እርምጃው ጥፋቱን እንዲገነዘብ ይረዳዋል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። (ከሕዝቅኤል 18:23 ጋር አወዳድር።) ሽማግሌዎች በክርስቶስ አመራር ሥር ሆነው ፍትሕን ያራምዳሉ፤ ይህም “ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ” መሆንን ይጨምራል። (ኢሳይያስ 32:1, 2) ስለዚህ አድልዎ የሌለበት ፍርድ መስጠትና ምክንያታዊ መሆን አለባቸው።—ዘዳግም 1:16, 17
ለመለኮታዊ ሥልጣን በታማኝነት ተገዙ
4 ፈራጅ ለመሆን ሕጉን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ከዚያም የሚበልጥ ብቃት ማሟላት ይጠይቃል። ሽማግሌዎቹ ፍጹማን ስላልነበሩ እንደ ራስ ወዳድነት፣ አድልዎና ስስት የመሰሉ የፍርድ አሰጣጥን ሊያጣምሙ የሚችሉ ግብረ ገብነት የጎደላቸውን ዝንባሌዎች ለማስወገድ ንቁ መሆን ነበረባቸው። ሙሴ “በፍርድም አድልዎ አታድርጉ፤ ታላቁን እንደምትሰሙ፣ ታናሹንም እንዲሁ ስሙ፤ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት አትፍሩ” ብሏቸዋል። አዎን፣ የእስራኤል ፈራጆች የሚፈርዱት ለአምላክ ነበር። ይህ ምንኛ በዓይነቱ ልዩ የሆነ መብት ነው!—ዘዳግም 1:16, 17፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የይሖዋ ማሳሰቢያዎች እምነት የሚጣልባቸው ናቸው
9 እስራኤላውያን “ጭልጥ ባለና በሚያስፈራ ምድረ በዳ” ውስጥ ያደረጉትን 40 ዓመት የፈጀውን አድካሚ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ይሖዋ እንዴት እንደሚመራቸው፣ እንደሚጠብቃቸውና እንደሚንከባከባቸው በዝርዝር አልነገራቸውም። ያም ሆኖ በእሱም ሆነ በሚሰጣቸው መመሪያዎች መታመን እንዳለባቸው የሚጠቁሙ ማስረጃዎችን በተለያዩ ጊዜያት አሳይቷቸዋል። ይሖዋ እስራኤላውያንን ለመምራት በቀን የዳመና ዓምድ በማታ ደግሞ የእሳት ዓምድ መጠቀሙ፣ አስቸጋሪ በሆነው የምድረ በዳ ጉዟቸው ወቅት ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሆነ አስታውሷቸዋል። (ዘዳ. 1:19፤ ዘፀ. 40:36-38) ከዚህም በተጨማሪ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን አሟልቶላቸዋል። “ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም።” በእርግጥም “ምንም ያጡት [ነገር] አልነበረም።”—ነህ. 9:19-21
ከሰኔ 7-13
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘዳግም 3–4
“የይሖዋ ሕጎች ጥበብ የሚንጸባረቅባቸውና ፍትሐዊ ናቸው”
it-2 1140 አን. 5
ማስተዋል
አንድ ሰው የአምላክን ቃል በትጋት ማጥናቱና ትእዛዛቱን ተግባራዊ ማድረጉ ከአስተማሪዎቹና ከሽማግሌዎች የበለጠ አስተዋይ እንዲሆን ያደርገዋል። (መዝ 119:99, 100, 130፤ ከሉቃስ 2:46, 47 ጋር አወዳድር።) ይህ የሆነው ጥበብና ማስተዋል በአምላክ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ላይ የተመሠረቱ ስለሆኑ ነው፤ እስራኤላውያን እነዚህን ድንጋጌዎች ቢታዘዙ በዙሪያቸው ባሉት ብሔራት ዘንድ “ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ” ተደርገው እንደሚቆጠሩ የተገለጸው ለዚህ ነው። (ዘዳ 4:5-8፤ መዝ 111:7, 8, 10፤ ከ1ነገ 2:3 ጋር አወዳድር።) አስተዋይ ሰው፣ የአምላክ ቃል ዝንፍ እንደማይል ይገነዘባል፤ አካሄዱ ከአምላክ ቃል ጋር የሚስማማ መሆን አለመሆኑን ይመረምራል፤ እንዲሁም በዚህ ረገድ እንዲረዳው አምላክን ይለምናል። (መዝ 119:169) የአምላክ መልእክት ውስጡ ዘልቆ እንዲገባ ያደርጋል (ማቴ 13:19-23)፤ በልቡ ጽላት ላይ ይጽፈዋል (ምሳሌ 3:3-6፤ 7:1-4)፤ እንዲሁም ‘ለሐሰት መንገድ ሁሉ’ ጥላቻ ያዳብራል (መዝ 119:104)። የአምላክ ልጅ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት በዚህ መንገድ አስተዋይ መሆኑን አሳይቷል፤ አሟሟቱን በተመለከተ በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተነገሩት ትንቢቶች መፈጸም እንዳለባቸው ስለሚያውቅ በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ ለመሞት እንኳ ፈቃደኛ ሆኗል።—ማቴ 26:51-54
የተትረፈረፈ ልግስና
ንግሥቲቱ በሰማችውና ባየችው ነገር እጅግ ተደንቃ በትህትና እንዲህ ስትል መለሰች፦ “በፊትህ ሁል ጊዜ የሚቆሙ ጥበብህንም የሚሰሙ ሰዎችና እነዚህ ባሪያዎችህ ምስጉኖች [“ደስተኛ፣” NW] ናቸው።” (1 ነገሥት 10:4-8) የሰሎሞን አገልጋዮች በሃብት የታጠሩ ቢሆኑም እንኳ ደስተኛ ያለቻቸው በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ በመገኘታቸው አልነበረም። ከዚህ ይልቅ የሰሎሞን አገልጋዮች አምላክ ለንጉሡ የሰጠውን ጥበብ ዘወትር የመስማት አጋጣሚ ስለነበራቸው የተባረኩ ነበሩ። የሳባ ንግሥት ዛሬ በፈጣሪና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ጥበብ ለሚደሰቱት የይሖዋ ሕዝቦች እንዴት ግሩም ምሳሌ ናት!
ንግሥቲቱ “አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን” ስትል ለሰሎሞን የተናገረችው ነገርም ልብ ሊባል የሚገባው ነው። (1 ነገሥት 10:9) ከሁኔታው ለመረዳት እንደሚቻለው የሰሎሞን ጥበብና ብልጽግና ከይሖዋ የተገኘ መሆኑን ተገንዝባለች። ይህም ቀደም ሲል ይሖዋ ለእስራኤል ከገባው ቃል ጋር የሚስማማ ነው። ‘ትእዛዜን ብትጠብቁ’ “በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና” ብሏቸው ነበር።—ዘዳግም 4:5-7
‘በአምላክ ዘንድ ሀብታም’ ነህ?
13 ይሖዋ ለሕዝቡ በረከቱን ሲያፈስ ሁልጊዜ የሚሰጣቸው ምርጡን ነው። (ያዕቆብ 1:17) ለምሳሌ ያህል፣ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ‘ምድር ማርና ወተት የምታፈስ’ ነበረች። የግብጽ ምድርም በዚህ መንገድ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ይሖዋ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ምድር ግን ቢያንስ በአንድ ወሳኝ መንገድ የተለየች ነበረች። ሙሴ ለእስራኤላውያን “ይህች ምድር አምላክህ እግዚአብሔር የሚንከባከባት . . . ናት” ብሏቸው ነበር። በሌላ አባባል ሕዝቡ፣ ይሖዋ ይንከባከባቸው ስለነበር ባለጠጎች ነበሩ። እስራኤላውያን ለይሖዋ ታማኝ ሆነው እስከቀጠሉ ድረስ ይሖዋ አትረፍርፎ ይባርካቸው የነበረ ሲሆን በዙሪያቸው ከሚገኙት ብሔራት ሁሉ የተሻለ ሕይወት እንዳላቸው በግልጽ ይታይ ነበር። በእርግጥም የይሖዋ በረከት “ብልጽግናን” ታመጣለች!—ዘኍልቍ 16:13፤ ዘዳግም 4:5-8፤ 11:8-15
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
የዘዳግም መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
4:15-20, 23, 24—ምስል መሥራት የተከለከለ መሆኑ የአንዳንድ ዕቃዎችን ምስል ሠርቶ በጌጥ መልክ መጠቀም ስህተት ነው ማለት ነው? አይደለም። ሕጉ የሚከለክለው ምስሎችን ለአምልኮ መሥራትን ይኸውም ለምስል ‘መስገድንና አምልኮ ማቅረብን’ ነው። ቅዱሳን ጽሑፎች በጌጣ ጌጥነት የሚያገለግሉ የአንዳንድ ነገሮችን ምስል መቅረጽ ወይም መሳል አይከለክሉም።—1 ነገሥት 7:18, 25
ከሰኔ 14-20
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘዳግም 5–6
“ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ እርዷቸው”
ወላጆች፣ የቤተሰባችሁን ፍላጎት አሟሉ
11 በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የዘዳግም 6:5-7ን ያህል ብዙ ጊዜ የሚጠቀስ ጥቅስ ያለ አይመስልም። እባካችሁ መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ገልጣችሁ ጥቅሱን አንብቡ። በመጀመሪያ ወላጆች ለይሖዋ ያላቸውን ፍቅር በመገንባትና ቃሉን በልባቸው በመያዝ የራሳቸውን መንፈሳዊነት እንዲንከባከቡ መታዘዛቸውን አስተውሉ። አዎን፣ መጽሐፍ ቅዱስን ዘወትር በማንበብ እንዲሁም የይሖዋን መንገዶች፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ሕጎች በትክክል መረዳትና መውደድ እንድትችሉ በዚያ ላይ በማሰላሰል የአምላክን ቃል በቁም ነገር ማጥናት ይኖርባችኋል። እንዲህ ስታደርጉ ልባችሁ አስደናቂ በሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ስለሚሞላ ደስታ የሚሰማችሁ ከመሆኑም ሌላ ለይሖዋ ጥልቅ አክብሮትና ፍቅር ያድርባችኋል። ለልጆቻችሁ የምትነግሯቸው ብዙ መልካም ነገሮች ታገኛላችሁ።—ሉቃስ 6:45
ልጆቼ በሚገባ የተማሩ እንዲሆኑ መርዳት የምችለው እንዴት ነው?
ምኞቶችህ፣ የምትመራባቸው ደንቦች፣ ከፍተኛ ግምት የምትሰጣቸው ነገሮችና ፍላጎቶችህ በምትናገረው ነገር ብቻ ሳይሆን በድርጊትህም ጭምር ይንጸባረቃሉ። (ሮሜ 2:21, 22) ልጆች ከጨቅላነታቸው አንስቶ የወላጆቻቸውን ድርጊት በጥንቃቄ በመመልከት ይማራሉ። ብዙውን ጊዜ ልጆች ወላጆቻቸው ከፍ አድርገው የሚመለከቷቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ስለሚገነዘቡ እነርሱም ተመሳሳይ አመለካከት ያዳብራሉ። ይሖዋን ከልብ የምትወድ ከሆነ ልጆችህ ይህን ያስተውላሉ። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት ከፍተኛ ቦታ እንደምትሰጥ ያያሉ። በሕይወትህ ውስጥ የአምላክን መንግሥት እንደምታስቀድም ይገነዘባሉ። (ማቴዎስ 6:33) በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ መገኘትህና የመንግሥቱን ምሥራች በመስበኩ ሥራ ላይ መካፈልህ፣ ለይሖዋ ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ ከምንም በላይ ከፍ አድርገህ የምትመለከተው ነገር መሆኑን እንዲያስተውሉ ያደርጋቸዋል።—ማቴዎስ 28:19, 20፤ ዕብራውያን 10:24, 25
ወላጆች፣ የቤተሰባችሁን ፍላጎት አሟሉ
14 ዘዳግም 6:7 እንደሚያሳየው እናንተ ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር መንፈሳዊ ነገሮችን መወያየት የምትችሉባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሉ። አብራችሁ ስትጓዙም ሆነ ሥራ ስትሠሩ ወይም አብራችሁ ስትዝናኑ የልጆቻችሁን መንፈሳዊ ፍላጎቶች ማሟላት የምትችሉባቸው አጋጣሚዎች ልታገኙ ትችላላችሁ። እንዲህ ሲባል ግን ለልጆቻችሁ ነጋ ጠባ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት “ንግግር” ትሰጣላችሁ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ ይልቅ በቤተሰባችሁ ውስጥ የሚኖረው ጭውውት ገንቢ የሆነ መንፈሳዊ ይዘት እንዲኖረው ጥረት አድርጉ። ለምሳሌ ያህል፣ ንቁ! መጽሔት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በርካታ ትምህርቶች ይዞ ይወጣል። እንደዚህ የመሳሰሉ ርዕሰ ጉዳዮች ይሖዋ ስለፈጠራቸው እንስሳት፣ በዓለም ዙሪያ ስለሚገኙ የሚያምሩ አካባቢዎች እንዲሁም ሰዎች ስላላቸው የተለያየ ባሕልና አኗኗር ለመነጋገር አጋጣሚ ሊከፍቱ ይችላሉ። እንዲህ ያሉት ውይይቶች ወጣቶች የታማኝና ልባም ባሪያ ክፍል የሚያዘጋጃቸውን ጽሑፎች በብዛት እንዲያነብቡ ሊያነሳሳቸው ይችላል።—ማቴዎስ 24:45-47
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ፍቅርና ፍትሕ—በጥንቷ እስራኤል ውስጥ
11 የምናገኘው ትምህርት፦ ይሖዋ ከውጫዊ ገጽታችን ባሻገር ያለውን ነገር የማየት ችሎታ አለው። ልባችንን ማለትም ውስጣዊ ማንነታችንን ይመለከታል። (1 ሳሙ. 16:7) ከእሱ ሊደበቅ የሚችል ምንም ዓይነት ሐሳብ፣ ስሜት ወይም ድርጊት የለም። ይሖዋ በውስጣችን ያለውን መልካም ነገር ያያል፤ እንዲሁም ያን መልካም ነገር ማሳደግ እንድንችል ይረዳናል። ሆኖም በልባችን ውስጥ ያለ መጥፎ አስተሳሰብ አድጎ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ከመፈጸማችን በፊት ይህን አስተሳሰብ ለይተን እንድናውቀውና እንድንቆጣጠረው ይፈልጋል።—2 ዜና 16:9፤ ማቴ. 5:27-30
ከሰኔ 21-27
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘዳግም 7–8
“ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ”
አምላክ፣ አገልጋዮቹ የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ብቻ እንዲያገቡ ያዘዘው ለምንድን ነው?
አንደኛ፣ ሰይጣን የአምላክ ሕዝቦች የሐሰት አማልክትን እንዲያመልኩ በማድረግ በቡድን ደረጃ ሊበክላቸው እንደሚፈልግ ይሖዋ ያውቃል። በመሆኑም አምላክ፣ የማያምኑ ሰዎች “እኔን ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ [ያደርጋሉ]” የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ይህ በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም። እስራኤላውያን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከጀመሩ የአምላክን ሞገስና ጥበቃ ያጣሉ፤ ይህም በቀላሉ በጠላቶቻቸው እጅ እንዲወድቁ ያደርጋል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ይህ ብሔር ተስፋ የተደረገውን መሲሕ እንዴት ሊያስገኝ ይችላል? በእርግጥም ሰይጣን፣ እስራኤላውያን ከማያምኑ ሰዎች ጋር እንዲጋቡ ለማድረግ የሚሞክርበት በቂ ምክንያት ነበረው።
“በጌታ ብቻ” ማግባት—በዘመናችንም ይቻላል?
ያም ሆኖ ይሖዋ፣ በጌታ ብቻ ማግባት እንዳለብን የሚገልጽ መመሪያ በቃሉ ውስጥ አስፍሮልናል። ለምን? ምክንያቱም ሕዝቦቹን የሚጠቅማቸውን ነገር ያውቃል። አገልጋዮቹ ጥበብ የጎደለው አካሄድ መከተል የሚያስከትለው ሥቃይ ውስጥ እንዳይገቡ ሊጠብቃቸው ብቻ ሳይሆን ደስተኞች እንዲሆኑም ጭምር ይፈልጋል። በነህምያ ዘመን ብዙ አይሁዳውያን፣ ይሖዋን የማያመልኩ የሌላ አገር ሴቶችን ያገቡ ነበር፤ በመሆኑም ነህምያ፣ የሰለሞንን መጥፎ ምሳሌነት ጠቀሰላቸው። ሰለሞን ‘በአምላኩ የተወደደ ሰው ቢሆንም ባዕዳን ሴቶች ወደ ኃጢአት መርተውታል።’ (ነህ. 13:23-26) እንግዲያው ይሖዋ፣ እውነተኛ አምላኪዎቹን ብቻ እንድናገባ ያዘዘን ለገዛ ጥቅማችን ሲል ነው። (መዝ. 19:7-10፤ ኢሳ. 48:17, 18) እውነተኛ ክርስቲያኖች አምላክ ለሚያሳያቸው ፍቅራዊ አሳቢነት አመስጋኞች ናቸው፤ እንዲሁም እሱ በሚሰጠው መመሪያ ይተማመናሉ። በዚህ መንገድ ለእሱ ሲገዙ የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዢ መሆኑን እንደሚቀበሉ ያሳያሉ።—ምሳሌ 1:5
በመጨረሻዎቹ ቀናት በጓደኛ ምርጫችሁ ጥንቃቄ አድርጉ
12 ማግባት የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ጓደኝነትን በተመለከተ ይበልጥ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። የአምላክ ቃል የሚከተለውን ግልጽ ምክር ይሰጣል፦ “ከማያምኑ ጋር አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ። ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ኅብረት አለው? ወይስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ያገናኘዋል?” (2 ቆሮ. 6:14) መጽሐፍ ቅዱስ፣ የትዳር ጓደኛ የሚፈልጉ የአምላክ አገልጋዮች “በጌታ ብቻ” እንዲያገቡ ይኸውም ራሱን ወስኖ የተጠመቀና በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች የሚመራ የይሖዋ አገልጋይ ብቻ እንዲያገቡ ይመክራል። (1 ቆሮ. 7:39) ክርስቲያኖች ከእምነት ባልንጀራቸው ጋር በትዳር ሲጣመሩ፣ ራሱን ለይሖዋ የወሰነና ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው እንዲመላለሱ የሚያግዛቸው አጋር ያገኛሉ።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
ይሖዋ ዕለታዊ ፍላጎታችንን ያሟላልናል
4 የዕለት እንጀራችንን ለማግኘት የምናቀርበው ጸሎት በየዕለቱ ለሚያስፈልገን መንፈሳዊ ምግብም ትኩረት እንድንሰጥ ሊያደርገን ይገባል። ኢየሱስ ለረጅም ጊዜ ከጾመ በኋላ በጣም ተርቦ የነበረ ቢሆንም ድንጋዩን እንጀራ እንዲያደርግ ሰይጣን ላቀረበለት ፈተና “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” ሲል መልሶለታል። (ማቴዎስ 4:4) ኢየሱስ እዚህ ላይ የጠቀሰው ሙሴ ለእስራኤላውያን የተናገረውን ሐሳብ ነበር፦ “ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፣ አስራበህም፣ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።” (ዘዳግም 8:3) ይሖዋ እስራኤላውያን መና እንዲያገኙ ያደረገበት መንገድ ሥጋዊ ምግብ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ መንፈሳዊ ትምህርት አስገኝቶላቸዋል። አንደኛ ነገር “ለዕለት ለዕለት የሚበቃቸውን ይልቀሙ” ተብለው ታዝዘው ነበር። ለዕለቱ ከሚበቃቸው በላይ ከሰበሰቡ የተረፈው መና መሽተትና መትላት ይጀምራል። (ዘጸአት 16:4, 20) ለሰንበት የሚያስፈልጋቸውን ጨምሮ እጥፍ አድርገው በሚሰበስቡበት በስድስተኛው ቀን ግን መናው አልተበላሸም። (ዘጸአት 16:5, 23, 24) ስለዚህ መና እንዲመገቡ የተደረገላቸው ዝግጅት ታዛዥ መሆን እንዳለባቸውና ሕይወታቸው በእንጀራ ላይ ብቻ ሳይሆን ‘ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ነገር ሁሉ’ ላይ የተመካ እንደሆነ የማይረሳ ትምህርት ሰጥቷቸዋል።
ከሰኔ 28–ሐምሌ 4
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘዳግም 9–10
“አምላክህ ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?”
ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
አምላክን በፈቃደኝነት ለመታዘዝ የሚያነሳሳን ምክንያት ምንድን ነው? ሙሴ አንደኛውን ምክንያት ሲገልጽ ‘አምላክህን ይሖዋን ፍራ’ ብሏል። (ቁጥር 12) ይህ ሲባል ቅጣት ይደርስብናል ብሎ በፍርሃት መራድ ማለት ሳይሆን ለአምላክና ለትእዛዛቱ አክብሮታዊ ፍርሃት ማሳየት ማለት ነው። ለአምላክ ጥልቅ አክብሮት ካለን እሱን የሚያሳዝን ነገር ላለማድረግ ጥረት እናደርጋለን።
ይሁን እንጂ አምላክን ለመታዘዝ በዋነኝነት የሚያነሳሳን ምክንያት ምን ሊሆን ይገባል? ሙሴ ‘አምላክህን ይሖዋን ውደደው፤ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ አገልግለው’ በማለት ተናግሯል። (ቁጥር 12) አምላክን መውደድ ከስሜት የበለጠ ነገር ይጠይቃል። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ “ስሜትን የሚገልጹ የዕብራይስጥ ግሶች አንዳንድ ጊዜ ስሜቱን ተከትሎ የሚመጣውን ድርጊት ጭምር ያመለክታሉ” ብሏል። ይኸው ጽሑፍ አምላክን መውደድ ሲባል እሱን “እንደምንወደው በሚያሳይ መንገድ መኖር” ማለት እንደሆነ ተናግሯል። በሌላ አባባል አምላክን ከልብ የምንወደው ከሆነ እሱን የሚያስደስተውን ነገር እናደርጋለን።—ምሳሌ 27:11
ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ለይሖዋ በፈቃደኝነት መታዘዛችን በረከት ያስገኝልናል። ሙሴ ‘መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞች ጠብቅ’ በማለት ጽፏል። (ቁጥር 13) አዎን፣ ይሖዋ ማንኛውንም ትእዛዝ የሚሰጠን ማለትም ከእኛ የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር እንድንፈጽም የሚጠብቅብን ለእኛ መልካም እንዲሆንልን በማሰብ ነው። እንዲህ ብለን ማመናችን ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ፍቅር ነው” ይላል። (1 ዮሐንስ 4:8) ይሖዋ እነዚህን ትእዛዛት የሰጠው ዘላቂ ጥቅም እንድናገኝ በማሰብ ብቻ ነው። (ኢሳይያስ 48:17) ይሖዋ እንድናደርግ ያዘዘውን ነገር ሁሉ መፈጸማችን በአሁኑ ወቅት ተስፋ ከሚያስቆርጡ ብዙ ችግሮች የሚጠብቀን ሲሆን ወደፊት ደግሞ መንግሥቱ ምድርን በሚያስተዳድርበት ጊዜ ማለቂያ የሌለው በረከት ያስገኝልናል።
በእርግጥ ‘ወደ አምላክ መቅረብ’ ትችላለህ?
2 በጥንት ዘመን የኖረው አብርሃም ከአምላክ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ነበረው። ይሖዋ ይህን የዕብራውያን አባት “ወዳጄ” ሲል ጠርቶታል። (ኢሳይያስ 41:8) አዎን፣ ይሖዋ አብርሃምን የግል ወዳጁ አድርጎ ተመልክቶታል። አብርሃም የአምላክ የቅርብ ወዳጅ የመሆን መብት ሊያገኝ የቻለው ‘በእግዚአብሔር ስላመነ’ ነው። (ያዕቆብ 2:23) በዛሬው ጊዜም ይሖዋ በፍቅር ተነሳስተው ከሚያገለግሉት ሰዎች ጋር ‘መወዳጀት’ ይፈልጋል። (ዘዳግም 10:15) የአምላክ ቃል “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” የሚል ማበረታቻ ይሰጠናል። (ያዕቆብ 4:8) ይህ ጥቅስ ይሖዋ ግብዣ እንዳቀረበልንና ቃል እንደገባልን የሚያሳይ ነው።
መንፈሳዊ ዕንቁዎች
it-1 103
ኤናቃውያን
በከነአን ተራራማ አካባቢዎች እንዲሁም በአንዳንድ የባሕር ዳርቻዎች (በተለይ በስተ ደቡብ በኩል) ይኖሩ የነበሩ እጅግ ግዙፍ ሕዝቦች ናቸው። በአንድ ወቅት አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ የተባሉ የታወቁ ኤናቃውያን በኬብሮን ይኖሩ ነበር። (ዘኁ 13:22) አሥራ ሁለቱ ዕብራውያን ሰላዮች ለመጀመሪያ ጊዜ ኤናቃውያንን ያዩት እዚሁ ኬብሮን ነው፤ ከዚያ በኋላ አሥሩ ሰላዮች ስላዩት ነገር የሚያስፈራ ወሬ ይዘው መጡ፤ በዚያ ያዩአቸው ኤናቃውያን ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩት የኔፍሊም ዝርያዎች እንደሆኑ እንዲሁም ዕብራውያኑ ከእነሱ አንጻር ሲታዩ ልክ እንደ “ፌንጣ” እንደሆኑ አወሩ። (ዘኁ 13:28-33፤ ዘዳ 1:28) የኤናቃውያን ግዝፈት እንደ ማነጻጸሪያ ተደርጎ ይጠቀስ ነበር፤ ግዙፍ የሆኑት ኤሚማውያን እና ረፋይማውያን እንኳ እንደ ኤናቃውያን እንደሆኑ ተገልጿል። ከግዝፈታቸው የተነሳ ሳይሆን አይቀርም “የኤናቅን ልጆች ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?” ተብሎ የሚነገር ምሳሌያዊ አባባል ነበር።—ዘዳ 2:10, 11, 20, 21፤ 9:1-3