ክርስቲያናዊ ሕይወት
የኢኮኖሚ ችግርን በልበ ሙሉነት መጋፈጥ
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት፣ ሕይወት በፈተና የተሞላ ነው። የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ እየተቃረበ ሲሄድ የሚያጋጥሙን ችግሮች መጨመራቸው አይቀርም። በአንዱ ወይም በሌላው እጦት ሊያጋጥመን ይችላል። (ዕን 3:16-18) ታዲያ የኢኮኖሚ ችግርን በልበ ሙሉነት ለመጋፈጥ ምን ይረዳናል? ምንጊዜም በአምላካችን በይሖዋ መታመን ይኖርብናል። እሱ አገልጋዮቹን እንደሚንከባከብ ቃል ገብቷል፤ ደግሞም በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን የሚያስፈልገንን ነገር ማሟላት ይችላል።—መዝ 37:18, 19፤ ዕብ 13:5, 6
ምን ማድረግ ትችላለህ?
መመሪያና ጥበብ እንዲሰጥህ እንዲሁም ድጋፍ እንዲያደርግልህ ይሖዋን ለምነው።—መዝ 62:8
ከዚህ በፊት ሠርተኸው የማታውቀው ሥራ ቢሆን እንኳ ለመሞከር ፈቃደኛ ሁን።—g 1/10 8-9 ሣጥኖች
ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ ይኑርህ፤ ይህም በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብን፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘትንና በአገልግሎት መካፈልን ይጨምራል
እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—“ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አንዳንድ ቤተሰቦች ምን ችግር ገጥሟቸዋል?
በሕይወት ውስጥ ከምንም በላይ አስፈላጊው ነገር ምንድን ነው?
የኢኮኖሚ ችግር ያጋጠማቸውን ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?