የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 ኅዳር ገጽ 11
  • የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት ተጠባበቁ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት ተጠባበቁ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በታላቁ መከራ’ ወቅት ታማኝነታችሁን ጠብቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • የአምላክ መንግሥት ጠላቶቹን ያጠፋል
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • አርማጌዶን—በጉጉት የምንጠብቀው ክንውን!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ይህ ዓለም ወደ ፍጻሜው የሚመጣው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 ኅዳር ገጽ 11
አንድ ወንድም “የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!” የተባለውን መጽሐፍ ሲያጠና። አንድ የይሖዋ መልአክ በአርማጌዶን ወቅት የተወሰኑ የአምላክ ሕዝቦችን ሲጠብቅ በዓይነ ሕሊናው ይሥላል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት ተጠባበቁ

በቅርቡ፣ ይሖዋ ለዚህ ዓለም የሚያሳየው ትዕግሥት ያልቃል። የሐሰት ሃይማኖት ይጠፋል፤ ግንባር የፈጠሩ ብሔራት በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት ይሰነዝራሉ፤ እንዲሁም ይሖዋ በአርማጌዶን ክፉዎችን ያጠፋል። ክርስቲያኖች እነዚህን አስደናቂ ክንውኖች በጉጉት ይጠባበቃሉ።

እርግጥ ነው፣ ስለ ታላቁ መከራ የማናውቃቸው ዝርዝር ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ የሚጀምርበትን ትክክለኛ ጊዜ አናውቅም። የፖለቲካ ኃይሎች በሃይማኖቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚጠቀሙበትን ሰበብ አናውቅም። ብሔራት በአምላክ ሕዝቦች ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እንዲሁም የትኞቹን ነገሮች እንደሚያካትት አናውቅም። በተጨማሪም ይሖዋ በአርማጌዶን ክፉዎችን ለማጥፋት የሚጠቀምበትን ዘዴ በእርግጠኝነት አናውቅም።

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በድፍረትና በልበ ሙሉነት ለመጠባበቅ የሚያስፈልጉንን መረጃዎች በሙሉ ይሰጠናል። ለምሳሌ የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ እንደሆነ እናውቃለን። (2ጢሞ 3:1) እውነተኛው ሃይማኖት እንዳይጠፋ ሲባል በሃይማኖቶች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ‘እንደሚያጥር’ እናውቃለን። (ማቴ 24:22) ይሖዋ ሕዝቦቹን እንደሚያድን እናውቃለን። (2ጴጥ 2:9) በተጨማሪም ይሖዋ ክፉዎችን ለማጥፋትና እጅግ ብዙ ሕዝብን ከአርማጌዶን ለማሻገር የሚጠቀምበት መሪ ጻድቅና ኃያል እንደሆነ እናውቃለን።—ራእይ 19:11, 15, 16

ወደፊት የሚመጡት ክንውኖች፣ ሰዎች ‘ከፍርሃት የተነሳ እንዲዝለፈለፉ’ እንደሚያደርጓቸው ጥያቄ የለውም። ይሁንና ይሖዋ በጥንት ጊዜ ሕዝቦቹን ስላዳነበት መንገድ እንዲሁም ስለ ወደፊቱ ጊዜ የነገረንን ነገር ካነበብንና ካሰላሰልን መዳናችን እየቀረበ እንደሆነ ተማምነን ‘ቀጥ ብለን መቆምና ራሳችንን ቀና ማድረግ’ እንችላለን።—ሉቃስ 21:26, 28

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ