የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ጥር ገጽ 3-16
  • ከጥር 8-14

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 8-14
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ጥር ገጽ 3-16

ከጥር 8-14

ኢዮብ 34–35

መዝሙር 30 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ሕይወት ፍትሐዊ እንዳልሆነ ሲሰማን

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ፈጽሞ ፍትሕ የጎደለው ነገር እንደማያደርግ አስታውሱ (ኢዮብ 34:10፤ wp19.1 8 አን. 2)

ክፉዎች ለሚያደርጉት ነገር ተገቢውን ቅጣት እንዳላገኙ ሊሰማን ይችላል፤ ሆኖም ከይሖዋ ሊደበቁ አይችሉም (ኢዮብ 34:21-26፤ w17.04 10 አን. 5)

ኢፍትሐዊ ድርጊት የተፈጸመባቸውን ሰዎች መርዳት የምንችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ እነሱን ስለ ይሖዋ ማስተማር ነው (ኢዮብ 35:9, 10፤ ማቴ 28:19, 20፤ w21.05 7 አን. 19-20)

አንድ ባልና ሚስት ከትላልቅ ሕንፃዎች አቅራቢያ በሚገኝ ደሳሳ ቤት ውስጥ ለሚኖር ሰውና ለልጁ ሲመሠክሩ።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 35:7—ኤሊሁ “[አምላክ] ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?” ብሎ ኢዮብን ሲጠይቀው ምን ማለቱ ነበር? (w17.04 29 አን. 3)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ኢዮብ 35:1-16 (th ጥናት 10)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ትናንሽ ልጆች ላሉት ሰው ከ​jw.org ላይ ለወላጆች የሚጠቅም መረጃ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 13 ነጥብ 5 (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 3)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 58

7. መደበኛ ባልሆነ መንገድ ‘ቃሉን መስበክ’ ትፈልጋለህ?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

አንዲት እህት አውቶቡስ ውስጥ ስልኳን ተጠቅማ ለአንዲት ሴት ስትመሠክር።

ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ቃሉን ስበክ፤ . . . በጥድፊያ ስሜት አገልግል” በማለት አበረታቶታል። (2ጢሞ 4:2) “በጥድፊያ ስሜት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ አገላለጽ ሁልጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ የሆነን በቦታው የተሰየመ ወታደር ወይም ዘብ ለማመልከት ተሠርቶበት ያውቃል። ይህ አገላለጽ፣ ከሰዎች ጋር በምንጨዋወትበት ጊዜ ሁሉ አጋጣሚውን ተጠቅመን ምሥክርነት ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን እንደምንፈልግ ጥሩ አድርጎ ይገልጻል።

ለይሖዋ ያለን ፍቅርና እሱ ላደረገልን መልካም ነገሮች ያለን አድናቆት የእሱን ግሩም ባሕርያት በተመለከተ ለሌሎች እንድንናገር ያነሳሳናል።

መዝሙር 71:8⁠ን አንብብ። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

የይሖዋን ጥሩነት በተመለከተ የትኞቹን ነገሮች ለሌሎች መናገር ትፈልጋላችሁ?

መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የሚያነሳሳን ሌላው ነገር ለሰዎች ያለን ፍቅር ነው።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን ሰሙ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን እንዲሰሙ ያስቻላቸው እንዴት ነው?

  • የቤተ ክርስቲያን አባል የነበሩት እነዚህ ሰዎች እውነትን መማራቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

  • ለሰዎች ያለን ፍቅር መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የሚያነሳሳን እንዴት ነው?

  • መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት ሌሎች ስለ ይሖዋ እንዲማሩ ለመርዳት የሚያስችል ውጤታማ መንገድ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 4 በገጽ 33 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 138 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ