የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ጥር ገጽ 12-13
  • ከየካቲት 19-25

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከየካቲት 19-25
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ጥር ገጽ 12-13

ከየካቲት 19-25

መዝሙር 8–10

መዝሙር 2 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ይሖዋ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ”!

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ለእኛ እጅግ ጥሩ ነው (መዝ 8:3-6፤ w21.08 3 አን. 6)

ስለ ይሖዋ ድንቅ ሥራዎች ለሌሎች በመናገር እሱን በደስታ እናወድሰዋለን (መዝ 9:1፤ w20.05 23 አን. 10)

በሙሉ ልባችን ለእሱ በመዘመርም እናወድሰዋለን (መዝ 9:2፤ w22.04 7 አን. 13)

ፎቶግራፎች፦ ይሖዋን ማወደስ የምንችልባቸው መንገዶች። 1. አንዲት አረጋዊት እህት ለምትንከባከባቸው ሴት ሲመሠክሩ። 2. ወንድሞችና እህቶች በስብሰባ ላይ ሲዘምሩ። 3. አንድ ትንሽ ልጅ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ሐሳብ ለመስጠት እጁን ሲያወጣ። 4. አንድ ወጣት ወንድም የስብሰባ አዳራሹን ሲያጸዳ። 5. አንዲት ወጣት እህት አብራት ለምትማር ልጅ ስትመሠክር።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ይሖዋን ማወደስ የምችልባቸው ሌሎች መንገዶች የትኞቹ ናቸው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 8:3—መዝሙራዊው ስለ አምላክ ጣቶች ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? (it-1 832)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 10:1-18 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የቤቱ ባለቤት በአምላክ እንደማያምን ነገረህ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ በአምላክ እንደማያምን ሆኖም ፈጣሪ መኖሩን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ለመመርመር ፈቃደኛ እንደሆነ ነግሮሃል። (th ጥናት 7)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) w21.06 6-7 አን. 15-18—ጭብጥ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ ይሖዋን እንዲያወድሱ እርዷቸው። (th ጥናት 10)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 10

7. ተፈጥሯዊ አነጋገር ተጠቅሞ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር የሚቻለው እንዴት ነው?

(10 ደቂቃ) ውይይት።

ለይሖዋ የምናቀርበውን ውዳሴ መጨመር የምንችልበት አንዱ መንገድ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ስንካፈል ለምናገኛቸው ሰዎች መመሥከር ነው። (መዝ 35:28) መደበኛ ባልሆን መንገድ ስለመመሥከር ስናስብ መጀመሪያ ላይ እንፈራ ይሆናል። ይሁንና ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ውይይት መጀመርና ማስቀጠል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ስንማር በዚህ የአገልግሎት መስክ ውጤታማ ልንሆን አልፎ ተርፎም ልንወደው እንችላለን!

“‘የሰላምን ምሥራች’ ለማወጅ ዝግጁ ሁኑ—ቅድሚያውን ውሰዱ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። አንዲት እህት ምግብ ቤት ውስጥ አጠገቧ ባለው ጠረጴዛ ላይ ከተቀመጠች ሴት ጋር ውይይት ስትጀምር።

“የሰላምን ምሥራች” ለማወጅ ዝግጁ ሁኑ—ቅድሚያውን ውሰዱ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ከዚህ አጭር ድራማ፣ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመመሥከር ረገድ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የሚረዳችሁ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

ቀጥሎ የቀረቡት ሐሳቦች ውይይት ለመጀመር ሊረዷችሁ ይችላሉ፦

  • ከቤታችሁ በወጣችሁ ቁጥር ውይይት ለመጀመር የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በንቃት ተከታተሉ። ስለዚህ ጉዳይ በመጸለይ ይሖዋ ቅን ልብ ወዳላቸው ሰዎች እንዲመራችሁ ጠይቁት

  • ተግባቢ ሁኑ፤ እንዲሁም ለምታገኟቸው ሰዎች ትኩረት ስጧቸው። የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ሊማርካቸው እንደሚችል ለመወሰን ስለ እነሱ ለማወቅ ጥረት አድርጉ

  • ሁኔታው አመቺ ከሆነ አድራሻ ለመለዋወጥ ሞክሩ

  • የመመሥከር አጋጣሚ ከማግኘታችሁ በፊት ጭውውቱ ቢያቆም ቅር አትሰኙ

  • ውይይታችሁ ካበቃ በኋላ ስለ ግለሰቡ አስቡ። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ወይም jw.org ላይ ወዳለ ርዕስ የሚመራ ሊንክ በመላክ ለግለሰቡ ትኩረት መስጠታችሁን ቀጥሉ

እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦ አንድ ሰው ‘ቅዳሜና እሁድ እንዴት ነበር?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ በስብሰባ ላይ የተማራችሁትን ነገር ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር ስለምታከናውኑት ሥራ ንገሩት።

8. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ

(5 ደቂቃ)

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 6 አን. 1-8 እና የክፍል 2 ማስተዋወቂያ

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 65 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ