የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መጋቢት ገጽ 10-11
  • ከሚያዝያ 8-14

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሚያዝያ 8-14
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መጋቢት ገጽ 10-11

ከሚያዝያ 8-14

መዝሙር 26–28

መዝሙር 34 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ንጉሥ ዳዊት አጥብቆ ሲጸልይ።

1. ዳዊት ንጹሕ አቋሙን ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ያጠናከረው እንዴት ነው?

(10 ደቂቃ)

ዳዊት ይሖዋ እንዲያጠራው ጠይቋል (መዝ 26:1, 2፤ w04 12/1 14 አን. 8-9)

ዳዊት ከመጥፎ ጓደኞች ርቋል (መዝ 26:4, 5፤ w04 12/1 15 አን. 12-13)

ዳዊት የይሖዋን አምልኮ ይወድ ነበር (መዝ 26:8፤ w04 12/1 16 አን. 17-18)


ዳዊት ስህተት የሠራባቸው ጊዜያት ቢኖሩም “በንጹሕ ልብ” ተመላልሷል። (1ነገ 9:4) ዳዊት ይሖዋን በሙሉ ልቡ ይወድና ያገለግል የነበረ መሆኑ ንጹሕ አቋም እንደነበረው ያሳያል።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 27:10—የቅርብ ጓደኞቻችን እንደተዉን ሲሰማን ይህ ጥቅስ የሚያጽናናን እንዴት ነው? (w06 7/15 28 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 27:1-14 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ ትራክት ተጠቀም። (th ጥናት 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ባበረከትከው ትራክት የጀርባ ገጽ ላይ በሚገኘው ጥያቄ ላይ ተወያዩ። ስለ jw.org ንገረው፤ ከዚያም በድረ ገጹ ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ነገሮች አሳየው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 3—ጭብጥ፦ የተበላሸው የምድር ሥነ ምህዳር ይስተካከላል። (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 128

7. ንጹሕ የሥነ ምግባር አቋም ያላቸው ወጣቶች

(15 ደቂቃ) ውይይት።

አንድ ወጣት ባነበበው ጥቅስ ላይ ሲያሰላስል። ከአጠገቡ “የወጣትነት ሕይወቴ—ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት እንድፈጽም የሚደረግብኝን ጫና መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ቪዲዮ የሚያሳይ ታብሌት አለ፤ ታብሌቱ ላይ ዮሴፍ ከጶጢፋር ሚስት ሲሸሽ ይታያል።

ክርስቲያን ወጣቶች የሥነ ምግባር ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ መታገል ያስፈልጋቸዋል። ፍጹም ካልሆነው ሥጋቸው ጋር ይታገላሉ፤ በተጨማሪም በአፍላ የጉርምስና ዕድሜ ላይ ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፤ በዚህ ዕድሜ ላይ የፆታ ስሜት ስለሚያይል የማመዛዝን ችሎታቸውን ሊያዛባው ይችላል። (ሮም 7:21፤ 1ቆሮ 7:36) ከዚህም ሌላ እኩዮቻቸው ተቃራኒም ሆነ ተመሳሳይ ፆታ ካላቸው ሰዎች ጋር የፆታ ብልግና እንዲፈጽሙ የማያባራ ተጽዕኖ ያሳድሩባቸዋል። (ኤፌ 2:2) ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ ወጣቶቻችንን እንኮራባቸዋለን።

የወጣትነት ሕይወቴ—ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት እንድፈጽም የሚደረግብኝን ጫና መቋቋም የምችለው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ኮሪ እና ካምሪን ምን ዓይነት የእኩዮች ተጽዕኖ አጋጥሟቸዋል?

  • ንጹሕ አቋማቸውን እንዲጠብቁ የረዳቸው ምንድን ነው?

  • አንተስ ተመሳሳይ ሁኔታ ቢያጋጥምህ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዱህ ይችላሉ?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 8 አን. 5-12

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 38 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ