የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ግንቦት ገጽ 2-3
  • ከግንቦት 6-12

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከግንቦት 6-12
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ግንቦት ገጽ 2-3

ከግንቦት 6-12

መዝሙር 36–37

መዝሙር 87 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “በክፉዎች አትበሳጭ”

(10 ደቂቃ)

ክፉዎች ብዙ ሥቃይና ጭንቀት ያደርሱብናል (መዝ 36:1-4፤ w17.04 10 አን. 4)

“በክፉዎች” ላይ መበሳጨታችንም ሊጎዳን ይችላል (መዝ 37:1, 7, 8፤ w22.06 10 አን. 10)

ይሖዋ በገባው ቃል ላይ መተማመናችን ሰላም ይሰጠናል (መዝ 37:10, 11፤ w03 12/1 13 አን. 20)

አንዲት እህት በጭንቀት ተውጣ ከስልኳ ላይ ዜና ስታነብ። በስልኳ ላይ ያሉት ምስሎች የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሰዎችን፣ ጉቦ የሚቀበልን ፖሊስ፣ ጠመንጃ የሚተኩሱ ወታደሮችን፣ በመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ያለን መሣሪያ የታጠቀ ሰው፣ የተሰረቁ ዕቃዎችን የተሸከሙ ዘራፊዎችን፣ ሕዝባዊ ዓመፅን እንዲሁም የመኪና አደጋ ከተከሰተ በኋላ እርዳታ ለመስጠት የመጡ ሰዎችን ያሳያሉ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ክፋትን ለሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች ከልክ ያለፈ ትኩረት እሰጣለሁ?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 36:6—መዝሙራዊው የይሖዋ ጽድቅ “ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች” [ወይም “እንደ አምላክ ተራሮች” ግርጌ] እንደሆነ ሲናገር ምን ማለቱ ሊሆን ይችላል? (it-2 445)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 37:1-26 (th ጥናት 10)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ከዚህ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኛ ያልነበረን ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwbv 45—ጭብጥ፦ የመዝሙር 37:4 ትርጉም ምንድን ነው? (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 33

7.‘ለመከራ ጊዜ’ ተዘጋጅታችኋል?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በተፈጥሯዊም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋዎች የተነሳ ብዙ መከራና ሐዘን ይደርስባቸዋል። (መዝ 9:9, 10) እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ‘የመከራ ጊዜ’ በየትኛውም ሰዓት ሊከሰት ይችላል፤ በመሆኑም ሁላችንም እንዲህ ላሉት ችግሮች መዘጋጀት ይኖርብናል።

በቁሳዊ ከመዘጋጀትa በተጨማሪ፣ አደጋ ሲከሰት ሁኔታውን ለመቋቋም ምን ሊረዳን ይችላል?

  • አእምሯዊ ዝግጅት አድርጉ፦ አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አምናችሁ ተቀበሉ፤ እንዲሁም በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቀድማችሁ አስቡ። ከቁሳዊ ንብረቶቻችሁ ጋር ከመጠን ያለፈ ቁርኝት እንዳይኖራችሁ ተጠንቀቁ። ይህም አፋጣኝ እርምጃ እንድትወስዱ እንዲሁም ከንብረቶቻችሁ ይልቅ ለደህንነታችሁና ለሕይወታችሁ ቅድሚያ እንድትሰጡ ይረዳችኋል። (ዘፍ 19:16፤ መዝ 36:9) በተጨማሪም አደጋ ከተከሰተ በኋላ ንብረታችሁን ብታጡ ከልክ በላይ እንዳታዝኑ ይረዳችኋል።—መዝ 37:19

  • መንፈሳዊ ዝግጅት አድርጉ፦ ይሖዋ እናንተን ለመንከባከብ ችሎታውም ሆነ ፍላጎቱ እንዳለው እምነት አዳብሩ። (መዝ 37:18) ‘ሕይወታችን ብቻ እንደ ምርኮ ሆኖ’ ቢሰጠን እንኳ ይሖዋ ምንጊዜም አገልጋዮቹን እንደሚመራቸውና እንደሚደግፋቸው አዘውትረን ማስታወስ ይኖርብናል፤ ይህን ማድረግ ያለብን አደጋ ከመድረሱ በፊት ነው።—ኤር 45:5፤ መዝ 37:23, 24

ይሖዋ በገባው ቃል ላይ ጠንካራ እምነት ካለን እሱን ‘በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያችን’ እናደርገዋለን።—መዝ 37:39

ሥዕሎች፦ “አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?” ከተባለው ቪዲዮ ላይ የተወሰዱ ሥዕሎች። 1. አንድ ወንድም መጽሐፍ ቅዱስ ሲያነብ። 2. ሱናሚ ሲከሰት። 3. ጥቅጥቅ ያለ ደመና። 4. ሰዎች ንብረታቸውን ተሸክመው በጎርፍ ውስጥ ሲጓዙ።

አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የተባለውን ሺዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • በአደጋ ጊዜ ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?

  • ለአደጋ ለመዘጋጀት የትኞቹን ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?

  • በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

ግብ

  • መጽሐፍ ቅዱስን በምታነቡበትና በምታጠኑበት ጊዜ ራሳችሁንም ሆነ ሌሎችን ለማጽናናት ልትጠቀሙባቸው የምትችሏቸውን ጥቅሶች ለማስተዋል ሞክሩ። እነዚህን ጥቅሶች JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ላይ በአንድ ፈርጅ ውስጥ ልታስቀምጧቸው ትችላላችሁ። ለምሳሌ jw.org ላይ በሚገኘው “መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ምን ይላል?” በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን ጥቅሶች ተመልከቱ።

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 9 አን. 8-16

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 57 እና ጸሎት

a ንቁ! ቁጥር 5 2017 ገጽ 4-6⁠ን ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ