የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ሐምሌ ገጽ 6-7
  • ከሐምሌ 22-28

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሐምሌ 22-28
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ሐምሌ ገጽ 6-7

ከሐምሌ 22-28

መዝሙር 66–68

መዝሙር 7 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ይሖዋ ሸክማችንን በየዕለቱ ይሸከምልናል

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ጸሎታችንን ይሰማል፤ መልስም ይሰጠናል (መዝ 66:19፤ w23.05 12 አን. 15)

ይሖዋ የተቸገሩ ሰዎች ለሚያስፈልጋቸው ነገር ትኩረት ይሰጣል (መዝ 68:5፤ w10 12/1 23 አን. 6፤ w09 4/1 31 አን. 1)

ይሖዋ በየዕለቱ ይረዳናል (መዝ 68:19፤ w23.01 19 አን. 17)

ሥዕሎች፦ አንዲት እህት በተለያዩ ጊዜያት ስትጸልይ። 1. ጠዋት ከአልጋ ስትነሳ። 2. ከልጆቿ ጋር፣ ትምህርት ቤት ከመሄዳቸው በፊት። 3. በሥራ ቦታዋ።

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ይሖዋ ሸክማችንን እንዲሸከምልን መፍቀድ የምንችለው እንዴት ነው?

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 68:18—በጥንቷ እስራኤል ዘመን ‘እንደ ስጦታ የሆኑ ሰዎች’ የተባሉት እነማን ናቸው? (w06 6/1 10 አን. 5)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 66:1-20 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የቤቱ ባለቤት ከአንተ የተለየ ባሕል አለው። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ባበረከትከው ትራክት ላይ ተመሥርተህ ውይይቱን ቀጥል። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 15 ማስተዋወቂያ እና ነጥብ 1-3 (th ጥናት 8)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 102

7. የወንድምህን ሸክም ማቅለል ትችል ይሆን?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

የአምላክ አገልጋዮች የሕይወትን ውጣ ውረድ ብቻቸውን መጋፈጥ አያስፈልጋቸውም። (2ዜና 20:15፤ መዝ 127:1) ይሖዋ ይረዳናል። (ኢሳ 41:10) ይሖዋ የሚረዳን በየትኞቹ መንገዶች ነው? በቃሉና በድርጅቱ አማካኝነት አመራር ይሰጠናል። (ኢሳ 48:17) ኃያል የሆነውን ቅዱስ መንፈሱን ይሰጠናል። (ሉቃስ 11:13) በተጨማሪም ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በማነሳሳት ማበረታቻና ተግባራዊ እርዳታ እንዲሰጡን ያደርጋል። (2ቆሮ 7:6) ከዚህ አንጻር ይሖዋ የወንድሞቻችንን ሸክም ለማቅለል ማናችንንም ሊጠቀም ይችላል።

“ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ለአረጋውያን” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። እህት ፓውሊና ሳንቲዝ ጎሜዞ ከቤቷ ውጭ ፈገግ ብላ ቆማ።

ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ለአረጋውያን የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የአንድን አረጋዊ ክርስቲያን ሸክም ለማቅለል ምን ማድረግ ትችላለህ?

“ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ጆሴፍ እና አኒታ ዴቪቶ አብረው ሲያገለግሉ።

ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ለሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የአንድን የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ሸክም ለማቅለል ምን ማድረግ ትችላለህ?

“ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ከሌላ አገር ለመጡ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ቢል እና ማጊ ዜንግ ፈገግ ብለው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያጠኑ።

ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በጉባኤ ውስጥ አሳዩ—ከሌላ አገር ለመጡ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • አስቸጋሪ ሁኔታ ያጋጠማቸውን ክርስቲያኖች ሸክም ለማቅለል ምን ማድረግ ትችላለህ?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 13 አን. 1-7፣ የክፍል 5 ማስተዋወቂያ እና በገጽ 103 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 88 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ