የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ሐምሌ ገጽ 4-5
  • ከሐምሌ 15-21

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሐምሌ 15-21
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ሐምሌ ገጽ 4-5

ከሐምሌ 15-21

መዝሙር 63–65

መዝሙር 108 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ‘ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ይሻላል’

(10 ደቂቃ)

ከአምላክ ጋር ያለን ጥሩ ግንኙነት ከሕይወት ይበልጥ ውድ ነው (መዝ 63:3፤ w01 10/15 15-16 አን. 17-18)

በይሖዋ ታማኝ ፍቅር መግለጫዎች ላይ ማሰላሰላችን ለእሱ ያለንን አድናቆት ያሳድገዋል (መዝ 63:6፤ w19.12 28 አን. 4፤ w15 10/15 24 አን. 7)

ለአምላክ ታማኝ ፍቅር ያለን አድናቆት እሱን በደስታ እንድናወድሰው ይገፋፋናል (መዝ 63:4, 5፤ w09 7/15 16 አን. 6)

ሥዕሎች፦ አንዲት እህት መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ። 1. ከአንዲት እህት ጋር አብራ በደስታ ስታገለግል። 2. በስብሰባ ላይ ሐሳብ ስትሰጥ።

ለቤተሰብ አምልኮ የሚሆን ሐሳብ፦ ይሖዋ ታማኝ ፍቅር ያሳያችሁ በየትኞቹ መንገዶች እንደሆነ ተወያዩ።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 64:3—ይህ ጥቅስ ንግግራችን የሚያንጽ እንዲሆን ለማድረግ የሚያነሳሳን እንዴት ነው? (w07 11/15 15 አን. 6)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 63:1–64:10 (th ጥናት 12)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የቤቱ ባለቤት የአንተን ቋንቋ መናገር አይችልም። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)

5. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ምሥክርነት መስጠት ከመቻልህ በፊት ውይይታችሁ ይደመደማል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)

6. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የግለሰቡን ትኩረት የሚስበው ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሞክር፤ ከዚያም ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ሁኔታዎችን አመቻች። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

7. እምነታችንን ማብራራት

(4 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq 51—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ከዚህ ቀደም “አልፈልግም” ያሉ ሰዎችን ድጋሚ የሚያነጋግሩት ለምንድን ነው? (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 3)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 154

8. ለአምላክ ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ ‘ታማኝ ፍቅሩ የበዛ’ አምላክ ነው። (መዝ 86:15) “ታማኝ ፍቅር” የሚለው አገላለጽ በከፍተኛ ቅንዓት፣ በጽኑ አቋም፣ በታማኝነትና ከልብ በመነጨ የመውደድ ስሜት ተነሳስቶ ፍቅር ማሳየትን ያመለክታል። ይሖዋ ለሁሉም ሰዎች ፍቅር የሚያሳይ ቢሆንም “ታማኝ ፍቅር” የሚያሳየው ለአገልጋዮቹ ማለትም ከእሱ ጋር ልዩ የሆነ ዝምድና ላላቸው ሰዎች ብቻ ነው። (መዝ 33:18፤ 63:3፤ ዮሐ 3:16፤ ሥራ 14:17) እኛም በምላሹ ለእሱ ፍቅር በማሳየት ለይሖዋ ታማኝ ፍቅር ያለንን አድናቆት ማሳየት እንችላለን። እንዴት? “ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ” የሚለውን ትእዛዝ ጨምሮ ትእዛዛቱን በመጠበቅ ነው።—ማቴ 28:19፤ 1ዮሐ 5:3

ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በአገልግሎታችሁ ላይ አሳዩ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

ፍቅር በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ምሥራቹን ለማካፈል የሚያነሳሳን እንዴት ነው?

    “ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በአገልግሎታችሁ ላይ አሳዩ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። አባትየው ከሥራ ተመልሶ ሶፋ ላይ እንቅልፍ ሲወስደው።
  • ሲደክመን

  • “ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በአገልግሎታችሁ ላይ አሳዩ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። አባትየው ከልጁ ጋር ሲያገለግል የሚያነጋግረው ሰው በቁጣ ሲመልስለት።
  • ተቃውሞ ሲያጋጥመን

  • “ለዘላለም የሚኖረውን ፍቅር በአገልግሎታችሁ ላይ አሳዩ” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። እናትየዋና ሴት ልጇ ሱፐር ማርኬት ውስጥ የምትሠራ ሴት ሲያነጋግሩ።
  • የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችንን ስናከናውን

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 12 አን. 14-20

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 79 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ