የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መስከረም ገጽ 10-11
  • ከጥቅምት 7-13

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥቅምት 7-13
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መስከረም ገጽ 10-11

ከጥቅምት 7-13

መዝሙር 92–95

መዝሙር 84 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ይሖዋን ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት ጎዳና ነው!

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ አምልኳችን ይገባዋል (መዝ 92:1, 4፤ w18.04 26 አን. 5)

ለሕዝቦቹ ወደር የሌለው ጥልቅ ማስተዋል ይሰጣቸዋል (መዝ 92:5፤ w18.11 20 አን. 8)

አገልጋዮቹ ባረጁ ጊዜም እንኳ ከፍ አድርጎ ይመለከታቸዋል (መዝ 92:12-15፤ w20.01 19 አን. 18)

ሥዕሎች፦ 1. አንዲት ወጣት ስትጸልይ። 2. ስትጠመቅ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ራሴን ለይሖዋ ወስኜ እንዳልጠመቅ ያገደኝ ምንድን ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 92:5—እነዚህ ቃላት የይሖዋን ጥበብ ጥሩ አድርገው የሚገልጹት እንዴት ነው? (cl 176 አን. 18)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 94:1-23 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የምታከናውነውን መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር ሥራ አስመልክቶ ለግለሰቡ ለመናገር የሚያስችል አጋጣሚ ፍጠር። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ቀደም ሲል መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ፈቃደኛ ያልነበረን ሰው ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) እድገት ከማያደርግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር የሚደረግ ውይይት። (lmd ምዕራፍ 12 ነጥብ 5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 5

7. ወጣቶች በጭንቀት ሲዋጡ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

አንዲት ወጣት ተስፋ በመቁረጥ መሬት መሬቱን ስታይ።

ይሖዋን የሚያገለግሉ ሰዎችም ከጭንቀት ነፃ የሆነ ሕይወት አይመሩም። ለምሳሌ ዳዊት በሕይወቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ጭንቀት አጋጥሞታል። በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ወንድሞቻችንም ጭንቀት ያጋጥማቸዋል። (መዝ 13:2፤ 139:23) የሚያሳዝነው፣ ወጣቶችም እንኳ በጭንቀት ሊዋጡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ የሚሰማቸው ጭንቀት ትምህርት ቤት እንደመሄድ ወይም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንደመገኘት ያሉ የተለመዱ እንቅስቃሴዎችም እንኳ በጣም እንዲከብዷቸው ሊያደርግ ይችላል። ምናልባትም ድንገተኛ የሆነ የመሸበር ስሜት ሊያድርባቸው፣ ይባስ ብሎም ራሳቸውን የማጥፋት ሐሳብ ሊመጣባቸው ይችላል።

ወጣቶች፣ ጭንቀት የሚያስቸግራችሁ ከሆነ ወላጆቻችሁን ወይም አንድን የጎለመሰ ሰው እርዳታ ጠይቁ። ይሖዋንም እንዲደግፋችሁ ጠይቁት። (ፊልጵ 4:6) እሱ ይረዳችኋል። (መዝ 94:17-19፤ ኢሳ 41:10) የስቲንግን ምሳሌ እንመልከት።

ይሖዋ ስለ እኔ ያስባል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

• ስቲንግን የረዳው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ነው? ለምንስ?

• ይሖዋ የተንከባከበው እንዴት ነው?

ባለፈው ሥዕል ላይ የታየችው ወጣት ስሜቷን ለወላጆቿ ስትገልጽ። ወላጆቿ በትኩረት እያዳመጧት ነው።

ወላጆች፣ ልጆቻችሁን በትዕግሥት በማዳመጥ፣ ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር በመግለጽ እንዲሁም ይሖዋ እንደሚወዳቸው እንዲተማመኑ በመርዳት ልጆቻችሁ ጭንቀትን እንዲቋቋሙ መርዳት ትችላላችሁ። (ቲቶ 2:4፤ ያዕ 1:19) ልጆቻችሁን ለመደገፍ የሚያስችል ብርታትና ጥንካሬ እንዲሰጣችሁ ይሖዋን ጠይቁት።

በጉባኤያችን ውስጥ ማን ከከባድ ጭንቀት ጋር እየታገለ እንዳለ አናውቅ ወይም ስሜቱን መረዳት አንችል ይሆናል። ያም ቢሆን፣ በጉባኤው ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ እንደምንወዳቸውና ከፍ አድርገን እንደምንመለከታቸው እንዲሰማቸው በማድረግ የበኩላችንን እርዳታ ማበርከት እንችላለን።—ምሳሌ 12:25፤ ዕብ 10:24

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 16 አን. 6-9፣ በገጽ 132 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 81 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ