የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መስከረም ገጽ 14-15
  • ከጥቅምት 28–ኅዳር 3

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥቅምት 28–ኅዳር 3
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መስከረም ገጽ 14-15

ከጥቅምት 28–ኅዳር 3

መዝሙር 103–104

መዝሙር 30 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “አፈር መሆናችንን ያስታውሳል”

(10 ደቂቃ)

የይሖዋ ርኅራኄ ምክንያታዊ እንዲሆን ያነሳሳዋል (መዝ 103:8፤ w23.07 21 አን. 5)

ስህተት በምንሠራበት ጊዜ ተስፋ አይቆርጥብንም (መዝ 103:9, 10፤ w23.09 6-7 አን. 16-18)

ከአቅማችን በላይ አይጠብቅብንም (መዝ 103:14፤ w23.05 26 አን. 2)

አንድ ባል፣ ሚስቱ ስሜቷን ስትገልጽ በጥሞና ሲያዳምጣት።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የትዳር ጓደኛዬን የምይዝበት መንገድ የይሖዋን ምክንያታዊነት የሚያንጸባርቅ ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 104:24—ይህ ጥቅስ ይሖዋ ስላለው የተለያዩ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታ ምን ያስተምረናል? (cl 55 አን. 18)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 104:1-24 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር ከተስማማ ሰው ጋር ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራምህ እንኳን ደህና መጣህ በሚለው ቪዲዮ ላይ ተወያዩ። (th ጥናት 9)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 6—ጭብጥ፦ ባል “ራሱን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱንም [መውደድ]” አለበት። (th ጥናት 1)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 44

7. የአቅም ገደባችሁን ታውቃላችሁ?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ ምርጣችንን ስንሰጠው ይደሰታል፤ እኛም እንደሰታለን። (መዝ 73:28) ይሁንና የአቅም ገደባችንን ከግምት ሳናስገባ ለይሖዋ ምርጣችንን ለመስጠት ከሞከርን ለአላስፈላጊ ጭንቀትና ለተስፋ መቁረጥ ልንዳረግ እንችላለን።

“ምክንያታዊ በመሆን ብዙ ነገር ማከናወን እንችላለን” በሚለው ቪዲዮ ላይ ያለችው ወጣት እህት።

ምክንያታዊ በመሆን ብዙ ነገር ማከናወን እንችላለን የተባለውን አጭር ድራማ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ይሖዋ ከእኛ የሚጠብቀው ምንድን ነው? (ሚክ 6:8)

  • “ምክንያታዊ በመሆን ብዙ ነገር ማከናወን እንችላለን” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ወጣቷ እህት ከጓደኛዋ ጋር ሆና በአንድ ሻይ ቤት ውስጥ አንዲትን ጥናት ስታበረታታ።
  • ወጣቷ እህት ግቧ ላይ ስለመድረስ ከልክ በላይ እንዳትጨነቅ የረዳት ምንድን ነው?

የአቅም ገደባችንን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

  • ራሳችሁን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ተቆጠቡ። (ገላ 6:4) ሌሎች የሚያከናውኑት ነገር እናንተ በምታከናውኑት ወይም ማከናወን እንደምትችሉ በምታስቡት ነገር ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር አትፍቀዱ። ማከናወን የምትችሉት ነገር ከእናንተ ጋር ተመሳሳይ ዕድሜ ወይም የቤተሰብ ሁኔታ ካለው ሰው የበለጠ ወይም ያነሰ ሊሆን ይችላል

  • አዲስ ነገር ለመሞከር ያላችሁ ፍርሃት አቅማችሁን እንዲገድበው አትፍቀዱ። (ሮም 12:1፤ 1ቆሮ 7:31) አንድ የአገልግሎት ዘርፍ መጀመሪያ ላይ ከአቅማችሁ በላይ እንደሆነ ወይም እንደማያስደስታችሁ ቢሰማችሁም እንኳ ከመሞከር ወደኋላ አትበሉ።—ሚል 3:10

  • የአጭር ጊዜ ግቦችን በማውጣት አቅማችሁን ፈትኑ። ለምሳሌ የዘወትር አቅኚ ሆናችሁ ለማገልገል አቅማችሁ ይፈቅድ ይሆን? ለተወሰኑ ወራት ያህል የአገልግሎት ሰዓታችሁን ከፍ ለማድረግ ወይም ረዳት አቅኚ ለመሆን ለምን አትሞክሩም? ለአንድ ዓመት ያህል በዘወትር አቅኚነት ማገልገል ትችሉ ይሆን? የዘወትር አቅኚ መሆን ወይም ከአንድ ዓመት በላይ በአቅኚነት ማገልገል እንደማትችሉ ብትደመድሙም እንኳ የአጭር ጊዜ ግቦቻችሁ ላይ በመድረሳችሁ ፈጽሞ አትቆጩም።—መክ 6:9

  • ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኞች ሁኑ። ያለንበት ሁኔታ ስለሚቀየር የአቅማችን ገደብም ይቀየራል። ስለዚህ በየተወሰነ ጊዜው ግቦቻችሁን መለስ ብላችሁ ገምግሙ

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 17 አን. 8-12፣ በገጽ 137 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 55 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ