የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ኅዳር ገጽ 2-16
  • ከኅዳር 4-10

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከኅዳር 4-10
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ኅዳር ገጽ 2-16

ከኅዳር 4-10

መዝሙር 105

መዝሙር 3 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ተስፋይቱ ምድር። ሥዕሎች፦ 1. አብርሃም። 2. ይስሐቅ። 3. ያዕቆብ።

1. “ቃል ኪዳኑን ለዘላለም . . . ያስታውሳል”

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ለአብርሃም ቃል ገብቶለት ነበር፤ ይህን ቃሉን ለይስሐቅና ለያዕቆብም ደግሞላቸዋል (ዘፍ 15:18፤ 26:3፤ 28:13፤ መዝ 105:8-11)

ይህ ቃል ሊፈጸም የማይችል ይመስል ይሆናል (መዝ 105:12, 13፤ w23.04 28 አን. 11-12)

ይሖዋ ለአብርሃም የገባውን ቃል ኪዳን ፈጽሞ አልረሳውም (መዝ 105:42-44፤ it-2 1201 አን. 2)


ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ይሖዋ እምነት የሚጣልበት አምላክ መሆኑን ማወቄ የሚጠቅመኝ እንዴት ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 105:17-19—“የይሖዋ ቃል” ዮሴፍን ያጠራው እንዴት ነው? (w86 11/1 19 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 105:24-45 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የቤቱ ባለቤት ሥራ ላይ ነው። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)

5. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መከራከር ሲጀምር ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 4 ነጥብ 5)

6. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ከዚህ በፊት ስትነጋገሩ የግለሰቡን ትኩረት ከሳበው ርዕሰ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ መጽሔት አበርክት። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)

7. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ስለ JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ንገረው፤ እንዲሁም አፕሊኬሽኑን እንዲያወርድ እርዳው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 84

8. የፍቅራችሁ መግለጫ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ገንዘባችንን ተጠቅመን የመንግሥቱን ሥራዎች ስንደግፍ ንጉሥ ሆኖ ለተሾመው ለይሖዋ ልጅ ለክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን ፍቅር እየገለጽን ነው። በዚህ መልኩ ፍቅራችንን መግለጻችን ይሖዋን ያስደስተዋል፤ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንንም ይጠቅማል። (ዮሐ 14:23) jw.org ላይ “የምታደርጉት መዋጮ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው እንዴት ነው?” በሚለው ዓምድ ሥር ያሉት ተከታታይ ርዕሶች፣ የምናደርገው መዋጮ ዓለም አቀፉን የወንድማማች ማኅበር በእጅጉ የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ያሳያሉ።

የአንድ ሰው እጅ ወደ መዋጮ ሣጥን ገንዘብ ሲከት። ሥዕሎች፦ 1. አንድ ወንድም ዳኛ ፊት ቆሞ። 2. አንዲት እህት በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ፕሮጀክት ስትካፈል። 3. አንዲት እህት የምልክት ቋንቋ ቪዲዮ ስትመለከት።

የምታደርጉት መዋጮ ኃይል አለው የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • በመዋጮ የተገኘው ገንዘብ ለሃይማኖት ነፃነታችን ለመሟገት መዋሉ ወንድሞቻችንን የጠቀማቸው እንዴት ነው?

  • ‘ሸክሙን እኩል መጋራት’ የስብሰባ አዳራሾችን ለመገንባት ያስቻለው እንዴት ነው?—2ቆሮ 8:14

  • በመዋጮ የተገኘው ገንዘብ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ በርካታ ቋንቋዎች የመተርጎሙን ሥራ ለመደገፍ መዋሉ ምን ጥቅም አስገኝቷል?

ኢንተርኔት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ሳንቲም የያዘ እጅ የሚያሳየው “መዋጮዎች“ የሚለው ገጽ አርማ።

የይሖዋ ምሥክሮች የሚያከናውኑትን ሥራ ለመደገፍ የፈቃደኝነት መዋጮ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? JW ላይብረሪ በተባለው አፕሊኬሽን መነሻ ገጽ ላይ ከታች የሚገኘውን “መዋጮዎች” የሚለውን ምልክት ተጠቀም። በብዙ አገሮች፣ “ጥያቄዎች” የሚለውን በመጫን ለይሖዋ ምሥክሮች የሚደረጉ መዋጮዎች—ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች የሚል ሰነድ ማግኘት ይቻላል።

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 17 አን. 13-19

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 97 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ