የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ኅዳር ገጽ 12-13
  • ከታኅሣሥ 23-29

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከታኅሣሥ 23-29
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ኅዳር ገጽ 12-13

ከታኅሣሥ 23-29

መዝሙር 119:121-176

መዝሙር 31 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከአላስፈላጊ የስሜት ሥቃይ ራሳችንን መጠበቅ

(10 ደቂቃ)

የአምላክን ትእዛዛት ውደዱ (መዝ 119:127፤ w18.06 17 አን. 5-6)

መጥፎ ድርጊትን ጥሉ (መዝ 119:128፤ w93 4/15 17 አን. 12)

ይሖዋን በመስማት “ተሞክሮ የሌላቸው” ሰዎች ከሚሠሩት ስህተት ተጠበቁ (መዝ 119:130, 133፤ ምሳሌ 22:3)

ከተደረደሩ የወርቅ ሳንቲሞችና ጥፍጥፍ ወርቆች አጠገብ የተገለጠ መጽሐፍ ቅዱስ።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የአምላክን ትእዛዛት በመውደድ ወይም መጥፎ ድርጊትን በመጥላት ረገድ የትኞቹን ማሻሻያዎች ማድረግ ያስፈልገኛል?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 119:160—ከዚህ ጥቅስ አንጻር ስለ ምን ነገር እርግጠኞች ልንሆን ይገባል? (w23.01 2 አን. 2)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 119:121-152 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ ትኩረቱን ሊስብ የሚችል መረጃ ከ​jw.org ላይ እንዴት ማግኘት እንደሚችል አሳየው። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ ከማይገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር የሚደረግ ውይይት። (lmd ምዕራፍ 12 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 121

7. ገንዘብ ለአላስፈላጊ ሥቃይ እንዲዳርጋችሁ አትፍቀዱ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

የገንዘብ ፍቅራቸውን ለማርካት የሚጣጣሩ ሰዎች “ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።” (1ጢሞ 6:9, 10) ገንዘብን የምንወድ ከሆነና ገንዘብ ማሳደድን የሕይወታችን ዓላማ አድርገን ከተነሳን ለብዙ አላስፈላጊ ሥቃይ እንዳረጋለን፤ ለምሳሌ፦

  • ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና መመሥረት አንችልም።—ማቴ 6:24

  • መቼም ቢሆን አንረካም።—መክ 5:10

  • እንደ ውሸት፣ ስርቆት እና ማጭበርበር ላሉ የሥነ ምግባር ፈተናዎች ይበልጥ እንጋለጣለን። (ምሳሌ 28:20) ለፈተናዎቹ እጅ ከሰጠን ደግሞ በበደለኝነት ስሜት እንዋጣለን፤ መልካም ስማችን ይበላሻል፤ እንዲሁም የአምላክን ሞገስ እናጣለን

“የገንዘብ አያያዝ” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። አንድ ወጣት የሳንቲም ማጠራቀሚያ ይዞ።

ዕብራውያን 13:5⁠ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የስሜት ሥቃይ እንዳይደርስብን ለገንዘብ ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ለምንስ?

የገንዘብ ፍቅር ባይኖረንም እንኳ ገንዘባችንን በአግባቡ ካልያዝን ለስሜት ሥቃይ እንዳረጋለን።

የገንዘብ አያያዝ የተባለውን የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

    “የገንዘብ አያያዝ” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። አንድ ወጣት ልጅና አንዲት ወጣት ልጅ የሚያስፈልጋቸውን ነገርና የሚፈልጉትን ነገር ዘርዝረው ይጽፋሉ፤ ከዚያም የእያንዳንዱን ነገር ዋጋ ይጽፋሉ። የወንዱ ልጅ ዝርዝር ውስጥ ሄድፎን፣ ጫማ፣ ምግብ እና የባቡር ቲኬት አለ። የሴቷ ልጅ ዝርዝር ውስጥ ቦርሳ፣ ሰዓት፣ ምግብ እና ነዳጅ አለ።
  • በጀት ማውጣት ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

  • “የገንዘብ አያያዝ” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ወጣቷ ልጅ በዝናብ ወቅት ሁለት ጥላ ትገዛለች። አንዱ ጥላ ለራሷ ሲሆን ሌላኛው ጥላ ደግሞ ለወንድሟ ነው፤ ወንድሟ ገንዘቡን አይስ ክሬም ገዝቶበታል።
  • የተወሰነ ገንዘብ መቆጠባችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

  • “የገንዘብ አያያዝ” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ሥዕል። ወጣቱ ልጅ ከግዙፍ ክሬዲት ካርድ ጋር በካቴና ታስሯል፤ ሌላ ክሬዲት ካርድ እየሳቀበት ነው።
  • አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ አለመግባት ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 20 አን. 1-7 እና የክፍል 7 ማስተዋወቂያ

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 101 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ