የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ኅዳር ገጽ 14-16
  • ከታኅሣሥ 30, 2024–ጥር 5, 2025

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከታኅሣሥ 30, 2024–ጥር 5, 2025
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ኅዳር ገጽ 14-16

ከታኅሣሥ 30, 2024–ጥር 5, 2025

መዝሙር 120–126

መዝሙር 144 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

እስራኤላውያን የተትረፈረፈ የስንዴ መከር በደስታ ሲሰበስቡ።

ወደ አገራቸው የተመለሱት እስራኤላውያን ይሖዋ ልፋታቸውን ስለባረከላቸው በደስታ ሲያጭዱ

1. በእንባ ዘርተው በእልልታ አጨዱ

(10 ደቂቃ)

እስራኤላውያን ከባቢሎን ነፃ ወጥተው ንጹሑን አምልኮ መልሰው ማቋቋም በመቻላቸው ተደስተው ነበር (መዝ 126:1-3)

ወደ ይሁዳ የተመለሱት ሰዎች ከሥራው ክብደት የተነሳ አልቅሰው ሊሆን ይችላል (መዝ 126:5፤ w04 6/1 16 አን. 10)

ሕዝቡ በመጽናታቸው ተባርከዋል (መዝ 126:6፤ w21.11 24 አን. 17፤ w01 7/15 18-19 አን. 13-14፤ ሥዕሉን ተመልከት)

እስራኤላውያን መሬቱን ለማረስ በትጋት ሲሠሩ። አንዱ ሰው ዘር ሲዘራ ሌላኛው መሬቱን ያርሳል።

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት ከዚህ አሮጌ ዓለም ከተገላገልን በኋላ በታላቁ የመልሶ ግንባታ ሥራ ወቅት የትኞቹ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል? የትኞቹን በረከቶችስ እናገኛለን?

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 124:2-5—ይሖዋ ለእስራኤል ብሔር እንዳደረገው ለእኛም አካላዊ ጥበቃ ያደርግልናል ብለን መጠበቅ እንችላለን? (cl 73 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 124:1–126:6 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን እንደሚከብደው ነግሮህ ነበር። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 16 ማስተዋወቂያ እና ነጥብ 1-3 (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 3)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 155

7. አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎች ተደሰቱ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ በባቢሎን በግዞት ለነበሩ ሕዝቦቹ የገባውን ቃል ፈጽሟል። ነፃ አውጥቷቸዋል፤ እንዲሁም በመንፈሳዊ ፈውሷቸዋል። (ኢሳ 33:24) ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ ሕዝቡ በግዞት በነበሩበት ወቅት በምድሪቱ ላይ ከተበራከቱት አንበሶችና ሌሎች አራዊት እነሱንም ሆነ የቤት እንስሶቻቸውን ጠብቋቸዋል። (ኢሳ 65:25) በገዛ ቤታቸው ውስጥ መኖርና ራሳቸው የተከሉትን ወይን ፍሬ መብላት ችለዋል። (ኢሳ 65:21) አምላክ ሥራቸውን ባርኮላቸዋል፤ ረጅም ዕድሜም ኖረዋል።—ኢሳ 65:22, 23

“አምላክ ስለ ሰላም በሰጣቸው ተስፋዎች ተደሰቱ—ተቀንጭቦ የተወሰደ” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ሥዕሎች። ሥዕሎች፦ 1. ወንድሞችና እህቶች አብረው ሲዝናኑ። 2. ተራሮችና ደኖች ከላይ ሲታዩ። 3. ነቢዩ ዳንኤል ከሞት ከተነሳ በኋላ ጫካ ውስጥ ሲሄድ። 4. አንድ ባልና ሚስት ከሞት የተነሳችውን ልጃቸውን ሲያቅፉ። 5. አትክልትና ፍራፍሬ የያዘ ሳህን። 6. ፏፏቴ።

Waterfall: Maridav/stock.adobe.com; mountains: AndreyArmyagov/stock.adobe.com

አምላክ ስለ ሰላም በሰጣቸው ተስፋዎች ተደሰቱ—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • እነዚህ ትንቢቶች በመንፈሳዊ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ እያየን ያለነው እንዴት ነው?

  • በአዲሱ ዓለም በላቀ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት እንዴት ነው?

  • በተለይ የትኛው ተስፋ ሲፈጸም ማየት ትፈልጋላችሁ?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 20 አን. 8-12፣ በገጽ 161 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 58 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ