የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ጥር ገጽ 2-3
  • ከጥር 6-12

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 6-12
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ጥር ገጽ 2-3

ከጥር 6-12

መዝሙር 127–134

መዝሙር 134 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ወላጆች—ውድ ውርሻችሁን መንከባከባችሁን ቀጥሉ

(10 ደቂቃ)

ወላጆች ቤተሰባቸውን ለመንከባከብ ይሖዋ እንደሚረዳቸው መተማመን ይችላሉ (መዝ 127:1, 2)

ልጆች ከይሖዋ የተገኙ ውድ ስጦታዎች ናቸው (መዝ 127:3፤ w21.08 5 አን. 9)

ለልጆቻችሁ ሥልጠና ስትሰጡ እያንዳንዱ ልጅ የሚያስፈልገውን ነገር ከግምት አስገቡ (መዝ 127:4፤ w19.12 27 አን. 20)

አንድ አባት “መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያዬ” የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ ሁለት ልጆቹን ሲያስጠና። ልጆቹ በገነት ውስጥ ከዝሆንና ከጎሪላ ጋር ሲጫወቱ በምናባቸው ይታያቸዋል።

ይሖዋ ወላጆች በእሱ በመታመን ልጆቻቸውን ለመንከባከብ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ሲያደርጉ ይደሰታል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 128:3—መዝሙራዊው ወንዶች ልጆችን ከወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ጋር ያመሳሰላቸው ለምንድን ነው? (w00 5/15 27 አን. 3-5)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 132:1-18 (th ጥናት 2)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ተናግሯል። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 16 ነጥብ 4-5። በሚቀጥለው ሳምንት አንተ ወደ ሌላ አካባቢ ብትሄድም ተማሪው ጥናቱን እንዲያጠና ስላደረግከው ዝግጅት ተወያዩ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 13

7. ወላጆች—ይህን ውጤታማ የማስተማሪያ መሣሪያ እየተጠቀማችሁበት ነው?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ይሖዋ እንዲያስተምሩ ለመርዳት የይሖዋ ድርጅት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሕትመት ውጤቶች አዘጋጅቷል። ያም ቢሆን፣ ወላጆች ሊጠቀሙባቸው ከሚችሏቸው በጣም ውጤታማ መሣሪያዎች አንዱ መልካም ምሳሌነታቸው ነው።—ዘዳ 6:5-9

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ይህን ውጤታማ መሣሪያ ተጠቅሞበታል።

ዮሐንስ 13:13-15ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን ማስተማሩ ውጤታማ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

ወላጆች፣ ድርጊታችሁ ለልጆቻችሁ በቃል ለምታስተምሩት ትምህርት ማጠናከሪያ ይሆናል። በተጨማሪም መልካም ምሳሌነታችሁ ልጆቻችሁ ለምታስተምሯቸው ትምህርት አክብሮት እንዲኖራቸው ያደርጋል፤ እንዲያዳምጧችሁም ያነሳሳቸዋል።

ሥዕሎች፦ “ምሳሌ በመሆን ልጆቻችንን አስተምረናል” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰዱ ሥዕሎች። 1. የወንድም ጋርሲያ ቤተሰቦች ወደ ጉባኤ ስብሰባ ለመሄድ መኪና ውስጥ ተቀምጠው። 2. ከስብሰባ ከተመለሱ በኋላ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው መክሰስ እየበሉ ሲጨዋወቱ። 3. ወንድም ጋርሲያ ጥናቱን አቋርጦ አንዷን ልጁን ሲያነጋግራት። 4. ወንድም ጋርሲያና ባለቤቱ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቅመው አንደኛዋን ልጃቸውን ሲያወያዩ።

ምሳሌ በመሆን ልጆቻችንን አስተምረናል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ወንድም ጋርሲያ እና ባለቤቱ ለልጆቻቸው የትኞቹን አስፈላጊ ትምህርቶች አስተምረዋል?

  • ይህ ቪዲዮ ለልጆቻችሁ መልካም ምሳሌ መሆናችሁን ለመቀጠል የሚያነሳሳችሁ እንዴት ነው?

መልካም ምሳሌ በመሆን ልጆቻችሁ የሚከተሉትን ነገሮች እንዲያደርጉ ማስተማር ትችላላችሁ፦

  • ከመዝናኛ፣ ከአልኮል መጠጥና ከማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርጉ

  • መንፈሳዊ ነገሮችን እንዲያስቀድሙ

  • ለትዳር ጓደኛቸው ፍቅርና አክብሮት እንዲያሳዩ

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 20 አን. 13-20

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 73 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ