ከሚያዝያ 28–ግንቦት 4
ምሳሌ 11
መዝሙር 90 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. አትናገሩ!
(10 ደቂቃ)
‘በባልንጀራችሁ’ ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ነገር አትናገሩ (ምሳሌ 11:9፤ w02 5/15 26 አን. 4)
ክፍፍል የሚፈጥር ነገር ከመናገር ተቆጠቡ (ምሳሌ 11:11፤ w02 5/15 27 አን. 2-3)
ሚስጥር አታውጡ (ምሳሌ 11:12, 13፤ w02 5/15 27 አን. 5)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ በሉቃስ 6:45 ላይ የሚገኘው ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ ጎጂ ንግግርን ለማስወገድ የሚረዳን እንዴት ነው?
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 11:17—ደግነት ማሳየታችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? (g20.1 11 ሣጥን)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 11:1-20 (th ጥናት 5)
4. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። በቅርቡ በስብሰባ ላይ ያገኘኸውን ትምህርት ለግለሰቡ ለመናገር አጋጣሚ ፈልግ። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 4)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ ቪዲዮ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)
6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ
(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምር ጋብዝ፤ እንዲሁም ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 3)
መዝሙር 157
7. አንደበታችሁ ሰላም እንዲያደፈርስ አትፍቀዱ
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ፍጹማን ስላልሆንን በንግግራችን መሳሳታችን አይቀርም። (ያዕ 3:8) ሆኖም ንግግራችን ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ማሰባችን በኋላ ላይ የምንጸጸትበትን ነገር ከመናገር እንድንቆጠብ ይረዳናል። የጉባኤውን ሰላም ሊያደፈርሱ ከሚችሉ አነጋገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ጉራ። እንዲህ ያለው ለራስ የሚቀርብ ውዳሴ ፉክክርና ቅናት ሊቀሰቅስ ይችላል።—ምሳሌ 27:2
ሐቀኝነት የጎደለው አነጋገር። እንዲህ ያለው አነጋገር ዓይን ያወጣ ውሸትን ብቻ ሳይሆን አንድን ሰው ለማታለል ተብሎ የሚነገርን ንግግር ያካትታል። ሐቀኝነትን በትንሹም እንኳ ማጓደል ሌሎች እምነት እንዳይጥሉብን ሊያደርግና መልካም ስማችንን ሊያበላሽ ይችላል።—መክ 10:1
ጎጂ ሐሜት። ሐሜት የሚባለው ስለ ሰዎች የሚነገር እውነት ያልሆነ ወይም የግል ሚስጥራቸውን የሚያጋልጥ ወሬ ነው። (1ጢሞ 5:13) እንዲህ ያለው አነጋገር ወደ ጠብና ወደ ክፍፍል ሊመራ ይችላል
ቁጣ። በአንድ ሰው ላይ ስንበሳጭ የምንናገረው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ንግግር ነው። (ኤፌ 4:26) እንዲህ ያለው አነጋገር ሰዎችን ይጎዳል።—ምሳሌ 29:22
ሰላም የሚያደፈርሱ ነገሮችን ‘አውልቃችሁ ጣሉ’—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
አነጋገራችን የጉባኤውን ሰላም በቀላሉ ሊያደፈርስ የሚችልበትን መንገድ በተመለከተ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
በጉባኤው ውስጥ መልሰው ሰላም ማስፈን የቻሉት እንዴት እንደሆነ ለማየት ‘ሰላምን ፈልጉ፤ ተከተሉትም’ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት።
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 25 አን. 14-21