ከግንቦት 12-18
ምሳሌ 13
መዝሙር 34 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. “የክፉዎች መብራት” አያታላችሁ
(10 ደቂቃ)
ክፉዎች ምንም የወደፊት ተስፋ የላቸውም (ምሳሌ 13:9፤ w03 9/15 24 አን. 5-6)
መጥፎ ነገሮችን ጥሩ አስመስለው ከሚያቀርቡ ሰዎች ጋር አትወዳጁ (ምሳሌ 13:20፤ w12 7/15 12 አን. 3)
ይሖዋ ጻድቃንን ይባርካል (ምሳሌ 13:25፤ w04 7/15 31 አን. 6)
ዓለማዊ ምኞቶችን የሚያሳድዱ ሰዎች ሕይወት ከውጭ እንደሚታየው አጓጊ አይደለም። የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉ ሰዎች ግን በሕይወታቸው እውነተኛ እርካታ ያገኛሉ
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
ምሳሌ 13:24—ይህ ጥቅስ ስለ ፍቅርና ስለ ተግሣጽ ምን ያስተምረናል? (w08 4/1 14 አን. 3-5)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) ምሳሌ 13:1-17 (th ጥናት 10)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ በማንሳት ከጀመርክ በኋላ የግለሰቡን ትኩረት ይበልጥ ስለሚስበው ሌላ ርዕሰ ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ አካፍል። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)
5. ውይይት መጀመር
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ በስብሰባችን ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)
6. ንግግር
(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 9—ጭብጥ፦ ወላጆቻቸውን የሚያከብሩና የሚታዘዙ ልጆች ይሳካላቸዋል። (th ጥናት 16)
መዝሙር 77
7. “የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል”
(8 ደቂቃ) ውይይት።
የአምላክ ቃል ወደር የለሽ እውቀትና ጥበብ ይዟል። በቃሉ ውስጥ በሚገኘው ብርሃን ሕይወታችንን ከመራን ዘላቂ ስኬትና ደስታ እናገኛለን። ዓለም እንዲህ ያለ ነገር ሊሰጠን አይችልም።
ዓለም የሌለውን ነገር ሊሰጣችሁ አይችልም የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
የእህት ጋይናንሽና ተሞክሮ “የጻድቃን ብርሃን” ‘ከክፉዎች መብራት’ ያለውን ብልጫ የሚያሳየው እንዴት ነው?—ምሳሌ 13:9
በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች ለማግኘት በመጎምጀት ወይም ይሖዋን ለማገልገል ስትሉ በከፈላችኋቸው መሥዋዕቶች በመቆጨት ጊዜ አታባክኑ። (1ዮሐ 2:15-17) ከዚህ ይልቅ ያገኛችሁት እውቀት ባለው “የላቀ ዋጋ” ላይ አተኩሩ።—ፊልጵ 3:8
8. ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ
(7 ደቂቃ)
9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 26 አን. 9-17