የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ግንቦት ገጽ 6-7
  • ከግንቦት 19-25

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከግንቦት 19-25
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ግንቦት ገጽ 6-7

ከግንቦት 19-25

ምሳሌ 14

መዝሙር 89 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. አደጋ ሲከሰት አካሄዳችሁን አንድ በአንድ አጢኑ

(10 ደቂቃ)

“ቃልን ሁሉ” አትመኑ (ምሳሌ 14:15፤ w23.02 23 አን. 10-12)

በራሳችሁ ስሜት ወይም ተሞክሮ ብቻ አትመሩ (ምሳሌ 14:12)

ከይሖዋ ድርጅት የሚመጣውን መመሪያ የሚቃወሙ ሰዎችን አትስሙ (ምሳሌ 14:7)

አንድ ቤተሰብ የJW ብሮድካስቲንግ ፕሮግራም አብሮ ሲመለከት።

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ሽማግሌዎች፣ አደጋ ሲከሰት መመሪያ ለመከተልና በይሖዋ ለመታመን ዝግጁ ናችሁ?—w24.07 5 አን. 11

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 14:17—“በጥሞና የሚያስብ ሰው አይወደድም” ሲባል ምን ማለት ሊሆን ይችላል? (w05 7/15 19 አን. 5-6)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ምሳሌ 14:1-21 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። የኢኮኖሚ ጉዳይ እንደሚያሳስበው ለነገረህ ሰው አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ አካፍል። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት የግለሰቡን ትኩረት ስቦት ስለነበረው ርዕሰ ጉዳይ የሚናገር መጽሔት አበርክት። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) ጥናትህ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ እንዲያነብ አበረታታው፤ እንዲሁም ግቡ ላይ መድረስ የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (th ጥናት 19)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 126

7. ምንጊዜም ለአደጋ ዝግጁ ሁኑ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በሽማግሌ የሚቀርብ። ቅርንጫፍ ቢሮው ወይም የሽማግሌዎች አካል የሰጡት ማሳሰቢያ ካለ ጥቀስ።

“በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ስንኖር ችግሮች እየተባባሱ እንደሚሄዱ እንጠብቃለን። (2ጢሞ 3:1፤ ማቴ 24:8) ብዙውን ጊዜ፣ አደጋ ሲከሰት የይሖዋ ሕዝቦች ወቅታዊና ሕይወት አድን የሆነ መመሪያ ይሰጣቸዋል። በዚያ ወቅት መትረፋችን የተመካው በአሁኑ ጊዜ በመንፈሳዊም ሆነ በቁሳዊ እንድንዘጋጅ የተሰጠንን መመሪያ በመታዘዛችን ላይ ሊሆን ይችላል።—ምሳሌ 14:6, 8

  • በመንፈሳዊ መዘጋጀት፦ ጥሩ መንፈሳዊ ልማድ አዳብሩ። በተለያዩ የአገልግሎት መስኮች ያላችሁን ክህሎት አሳድጉ። ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከጉባኤያችሁ ወንድሞች ለመነጠል ብትገደዱ አትሸበሩ። (ምሳሌ 14:30) ምንም ነገር ከይሖዋ አምላክና ከክርስቶስ ኢየሱስ ሊለያችሁ አይችልም።—od 176 አን. 15-17

  • በቁሳዊ መዘጋጀት፦ ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ቦርሳ ከማዘጋጀት በተጨማሪ እያንዳንዱ ቤተሰብ የተወሰነ ምግብ፣ ውኃ፣ መድኃኒትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ አለበት፤ ምክንያቱም በአደጋው ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ ከቤት ሳይወጡ መቆየት ሊያስፈልግ ይችላል።—ምሳሌ 22:3፤ g17.5 4

ቀደም ባለው ሥዕል ላይ የታየው ቤተሰብ አባላት የአደጋ ጊዜ ቁሳቁስ ሲያዘጋጁ።

አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • በአደጋ ጊዜ ይሖዋ የሚረዳን እንዴት ነው?

  • ለአደጋ ለመዘጋጀት የትኞቹን ተግባራዊ እርምጃዎች መውሰድ እንችላለን?

  • በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

‘በቅርቡ ካጋጠሙ የተፈጥሮም ሆኑ ሰው ሠራሽ አደጋዎች ዝግጁነትን በተመለከተ ምን ትምህርት አግኝቻለሁ?’

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 26 አን. 18-22፣ በገጽ 209 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 116 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ