የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ግንቦት ገጽ 12-13
  • ከሰኔ 16-22

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከሰኔ 16-22
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ግንቦት ገጽ 12-13

ከሰኔ 16-22

ምሳሌ 18

መዝሙር 90 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከጤና እክል ጋር የሚታገሉ ሰዎችን በንግግራችሁ አበረታቱ

(10 ደቂቃ)

አምላካዊ ጥበብ በሚንጸባረቅበት መንገድ ተናገሩ (ምሳሌ 18:4፤ w22.10 22 አን. 17)

ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት ጥረት አድርጉ (ምሳሌ 18:13፤ mrt ርዕስ 19 ሣጥን)

የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ስጧቸው፤ እንዲሁም ታጋሽ ወዳጅ ሁኑ (ምሳሌ 18:24፤ wp23.1 14 አን. 3–15 አን. 1)

አንድ ባል ሚስቱ ስሜቷን ስትገልጽ በጥሞና ሲያዳምጣት።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የትዳር አጋሬ ከአካላዊ ወይም ከአእምሯዊ ሕመም ጋር እየታገለ ከሆነ ልደግፈው የምችለው እንዴት ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 18:18—በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ዕጣ ጥቅም ላይ የሚውለው ለምን ነበር? (w07 7/15 12 አን. 4)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ምሳሌ 18:1-17 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ነው። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ መልእክትህን እንድታሳጥር ይጠይቅሃል። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 4)

6. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ስለ አምላክ መንግሥት አንድ ወሳኝ እውነት አስተምረው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)

7. እምነታችንን ማብራራት

(4 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwbq ርዕስ 123—ጭብጥ፦ አምላክ በሁሉም ቦታ ይገኛል? (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 5)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 144

8. ቤተሰቦቻችን ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡ “ያለቃል” መርዳት

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ብዙዎቻችን በአሁኑ ወቅት ይሖዋን እያገለገለ ያልሆነ ሰው እናውቃለን፤ ምናልባትም ግለሰቡ የትዳር አጋራችን፣ ልጃችን ወይም ከጉባኤ የራቀ ጓደኛችን ሊሆን ይችላል። እንዲህ ያለው ሰው ይሖዋን እንዲያገለግል ካለህ ጉጉት የተነሳ ግለሰቡን ለመጫን ወይም አክብሮት በጎደለው መንገድ ለመናገር ተፈትነህ ታውቃለህ? ይህን የምናደርገው በቅንነት ቢሆንም እንኳ ንግግራችን ነገሮችን ሊያባብስ ይችላል። (ምሳሌ 12:18) ታዲያ ምን ብናደርግ የተሻለ ይሆናል?

አንደኛ ጴጥሮስ 3:1 አማኝ ያልሆነ ባል ‘ያለቃል ሊማረክ’ እንደሚችል ይናገራል። የአንዲት እህት ባል ከሚስቱ ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ለመወያየት ፈቃደኛ ባይሆንም እንኳ ይሖዋን እንዲያውቅ ልትረዳው ትችል ይሆናል። እንደ ፍቅር፣ ደግነትና ጥበብ ያሉ ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ማንጸባረቋ የባሏን ልብ ሊያለሰልሰው ይችላል። (ምሳሌ 16:23) ምግባራችንና ለዛ ያለው አነጋገራችን በአሁኑ ወቅት ይሖዋን በማያገለግሉ ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችን ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።—ቆላ 4:6

ለእምነት ብርቱ ትግል በማድረግ የተሳካላቸው—የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላቸው የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

    “ለእምነት ብርቱ ትግል በማድረግ የተሳካላቸው—የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላቸው” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። እህት ሂዴኮ ሳሳኪ።
  • ከእህት ሳሳኪ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

  • “ለእምነት ብርቱ ትግል በማድረግ የተሳካላቸው—የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላቸው” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። እህት ኖሪኮ ኢቶ።
  • ከእህት ኢቶ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

  • “ለእምነት ብርቱ ትግል በማድረግ የተሳካላቸው—የማያምን የትዳር ጓደኛ ያላቸው” ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። እህት ቶሞኤ ኦካዳ።
  • ከእህት ኦካዳ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 27 አን. 23-26፣ በገጽ 214, 217 ላይ ያሉት ሣጥኖች

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 60 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ